አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሎት 1 የተለያዩ የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ ሎት 2 የውሃ እቃዎች፣ ሎት 3 ጀኔሬተርና ተርባይኖች እስከመግጠም ስራ(Installation) እና ፓምፕ፣ ሎት 4 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች እና ሎት 5 ሲሚንቶ የማጓጓዝ ትራንስፖርት አገልግሎት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Abay Construction (አባይ ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማህበር)
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አኮኃ/የተ/የግ/ማ/ብግጨ/01/19
አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሎት 1 የተለያዩ የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ ሎት 2 የውሃ እቃዎች፣ ሎት 3 ጀኔሬተርና ተርባይኖች እስከመግጠም ስራ(Installation) እና ፓምፕ፣ ሎት 4 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች እና ሎት 5 ሲሚንቶ የማጓጓዝ ትራንስፖርት አገልግሎት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ድርጅቱ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።
- የሚገዙ እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 16 ድባንቄ መድሀኒያለም ቤተክርስቲያን ሀዳሴ ሰፈር ታክስ ማዞሪያ 190 ሜትር አልፍ ብሎ አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ በግዥና አቅርቦት የስራ ክፍል የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች በየሎቱ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በአባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት የጨረታውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ትክክለኛ ስምና አድራሻ በመፃፍ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 15ኛው ቀን 8:00 ሰዓት በስራ ሰዓት በግዥና አቅርቦት የስራ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
- ለሎት 3 እና ሎት 4 ቴክኒካልና ፋይናንሻል በተለያየ በታሸገ ፖስታ ትክክለኛ ስምና አድራሻ በመፃፍ ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ በ8:00 ሰዓት ይዘጋል፤ በ15ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና አቅርቦት የስራ ክፍል ቢሮ ይከፈታል።
- 15ኛው ተከታታይ ቀን የበዓላት ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከግዥና አቅርቦት የስራ ክፍል ድረስ በአካል በመገኘት ወይም https://www.abayconstruction.org.et/aution-bid/ ማግኘት ይቻላል።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር: 0912993321 / 0918490526 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር
✨ messages.ai_summary
Abay Construction invites bids for five lots: construction materials, water materials, generators/turbines with installation and pumps, laptops, and cement transport services. Bidders must submit a valid trade license, TIN, and VAT registration certificate. Lots 3 and 4 require separate technical and financial envelopes.
