የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በሚ/አ/ከ/አስ/ር ስር ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገ/ት የሚውሉ ፈርኒቸር ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ /ኢ/ል/ጽ/ቤት
በድጋሚ የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በሚ/አ/ከ/አስ/ር ስር ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገ/ት የሚውሉ ፈርኒቸር ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላል።
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው
- በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ኦንላይን የተመዘገቡና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- ግብር ስለመክፈላቸው ከገቢዎች መ/ቤት ክሊራንስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ ሰነድ ከግዥ ኬዝ ቲም የሥራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን /በነጻ/ በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱ ሞልተው ሲመልሱ ህጋዊነት ሰነድ እና ፋይናንሻል የተሞላበትን ሰነድ 1 ኦርጅናልና 1 ኮፒ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ 20,000/ሃያ ሺ ብር/ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ቼክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ለሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በማለት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3:30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ4:00 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
- ሰነዱን ሞልተው ወደ ጨረታ ሳጥን ለማስገባት ሲመጡ ተመዝግበውና ፈርመው ማስገባት አለባቸው
- በጨረታ ማስታወቂያ ላይ የቃላት ወይም የትርጉም ስህተት ቢኖር በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጠው የበለጠ ተቀባይነት ይኖረዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Mizan Aman City Administration Finance Office seeks bidders to supply furniture for its sub-offices. Bidders must have a renewed business license, VAT registration, online supplier registration certificate, TIN, and tax clearance. Bid documents are free from the procurement office.
