Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Rural Roads Construction Agency (የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ)
  • Address ባህርዳር ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-222-11-00
  • Website
  • Deadline02 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 500.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityየጠቅላላ ዋጋ 1% (ከፍተኛው ብር 2,000,000.00) CPO ወይም የባንክ ዋስትና
  • opening date21/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:30
  • Categories Building Materials

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል የስሚንቶ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ በጠቅላላ ድምር /በጥቅል/ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Amhara Rural Roads Construction Agency (የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ)


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 04/2019

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል የስሚንቶ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ በጠቅላላ ድምር /በጥቅል/ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ለውድድር ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፤
  3. ተጫራቾች የሚጠበቅባቸውን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው ፡፡
  4. የግዥው መጠን ከብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  5. የሚገዛ የስሚንቶ ዝርዝር መግለጫ /specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመ/ቤቱ አካውንት ቁጥር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 በመክፈል የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ 11/02/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ቀን 21/02/2019 ዓ.ም ማግኘት ይቻላል፤
  7. ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን ማለትም ዋናና ኮፒ (Original and Copy) በማለት በአንድ ኢንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት /በአየር ላይ ከዋለበት/ ቀን ከ11/02/2019 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ቀን 21/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል
  8. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትና ሌሎች ታክስ እንዲሁም የትራንስፖርት ዋጋን ጨምሮ መሆን አለበት ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የስሚንቶ ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፤ ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 2,000,000.00 /ሁለት ሚሊዮን ብር/ የሚበልጥ ከሆነ 2,000,000.00 /ሁለት ሚሊዮን ብር/ ብቻ ማስያዝ ይችላሉ
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በቀን 21/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 8:30 ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል፤
  10. የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  11. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የዋጋ መሙያ ገፅ ላይ ፊርማና መህተም ማድረግ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም በዋጋ መሙያው ላይ ስርስ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
  12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058-222-1100 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058-322-5155 /058-222-1101 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  13. ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ

✨ messages.ai_summary
Amhara Rural Roads Construction Agency seeks to buy cement through open tender for its road construction and maintenance works. Bidders must have a valid trade license, TIN, proof of tax payment, and VAT registration if the purchase exceeds ETB 500,000. Detailed cement specifications are in the tender document.
Save Tender