Tender Detail

Tender Details

  • Company Oromia Police Commission (የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን)
  • Address የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አ/አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ ላንቻ አካባቢ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0913 108 990
  • Websitehttps://oromiapolice.gov.et/am/
  • Deadline06 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 200 (የማይመለስ)
  • Bid Securityየየሎቱ 2% (እስከ ብር 500,000) CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ
  • opening date27/02/2019 ዓ.ም በ4:30 ሰዓት
  • Categories Car Decoration Materials , Tire And Spare Parts , Vehicle Spare Parts

የመኪና መለዋወጫ፣ የመኪና ማስዋቢያ ዕቃዎች እና የመኪና ባትሪዎች ግዥ (3 ሎቶች, ግ/ጨ/03/2019) - የኦሮሚያ ፖሊስ ጠቅላይ ዋና መምሪያ

Oromia Police Commission (የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን)


በኦሮሚያ ፖሊስ ጠቅላይ ዋና መምሪያ የተዘጋጀ
ግ/ጨ/03/2019 የበጀት ዓመት

የኦሮሚያ ፖሊስ ጠቅላይ ዋና መምሪያ በ2019 የበጀት ዓመት ለክልሉ ፖሊስ ስራ አገልግሎት ላይ የሚውል የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የመኪና ማስዋቢያ ዕቃዎች እና የመኪና ባትሪዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት የግዥው አይነት፡-
ሎት አንድ፡-የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች
ሎት ሁለት፡-የተለያዩ የመኪና ማስዋቢያ ዕቃዎች
ሎት ሶስት፡-የተለያዩ የመኪና ባትሪዎች

በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት በዘርፉ የተሰማሩ ብቃት ያላቸው ተወዳዳሪዎችን ለዉድድር ይጋብዛል።

  1. ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ስለመከፈላቸው የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
  3. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  4. ማንኛውም ተወዳዳሪ የሚወዳደርበት ዕቃ አንድ አንድ ናሙና (ሳምፕል) ማቅረብ አለባቸው።
  5. ናሙና (ሳምፕል) ያለቀረበ ተወዳዳሪ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የየሎቱ ለየብቻ 2% ሆኖ የሚያስዙት ዋስትና ከ500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ብር ብቻ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  7. የጨረታ ሰነዱ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 (አስራ አምስት) ቀናት ከፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
  8. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎችን በራሱ ወጪ የማጓጓዣ፣መጫኛ እና ውረጃ ወጪዎችን ሸፍነው ቢሾፍቱ የሚገኘው የኦሮሚያ ፖሊስ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  9. ማንኛውም ተወዳዳሪ የመወዳደሪያ ሰነዱ ሲያዘጋጅ እና ሲያስገባ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በመለየት ማቅረብ ይጠበቅበታል፤ ማለትም ቴክኒካል ኦርጅናል፣ ቴክኒካል ኮፒ፣ ፋይናንሻል ኦርጅናል፣ ፋይናንሻል ኮፒ እና ሲፒኦ ወይም ጋራንቲ ለየብቻ በማሸግ ሁሉንም ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለበት። ይህንን ያላሟላ ተወዳዳሪ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።
  10. ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሰነዱ ሲያዘጋጅ ቫት እና ማንኛውንም ወጭን ጨምሮ መሙላት አለበት ይህ ካልሆነ የቀረበ ዋጋ ሁሉንም ወጪዎች አካቶ እንደተሞላ ተደርጎ ይቆጠራል።
  11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀን ገደብ 27/02/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ይሆናል።
  12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 27/02/2019 ዓ.ም በኦሮሚያ ፖሊስ ግዥ አገልግሎት መምሪያ ውስጥ በ4:30 ሰዓት ይከፈታል።
  13. ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኦሮሚያ ፖሊስ፡-
አድራሻ፡-ኦሮሚያ ፖሊስ አ/አበባ ክ/ከተማ ቂርቆስ ላንቻ አካባቢ
ለተጨማሪ መረጃ፡-0913108990 ወይም 0996054778 መደወል ይችላሉ

የኦሮሚያ ፖሊስ ጠቅላይ ዋና መምሪያ

✨ messages.ai_summary
Oromia Police Commission seeks qualified suppliers for vehicle spare parts, car care products, and vehicle batteries, split into three lots. Bidders need a valid trade license, tax payment proof, supplier registration, and a sample per item.
Save Tender