Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address አዳማ ከተማ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 022-211-14-42
  • Website
  • Deadline04 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 500.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityለእያንዳንዱ ጨረታ ብር 50,000.00 (CPO)
  • opening dateበዚዉ ቀን በ4:30
  • Categories Electronics Materials

የአዳማ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማዉ መስተዳደር ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2019 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ለመግዛት በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የአዳማ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማዉ መስተዳደር ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2019 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ለመግዛት በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለዉ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣የዘመኑን ግብር ከፍሎ ማጠናቀቁንና፣ጨረታ ላይ እንዲሳተፍ የሚል ማስረጃ ከሀገር ዉስጥ ገቢ ባለስልጣን ጽ/ቤት ማቅረብ አለበት፡፡
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT ) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጽ/ቤቱ ስም ሲንቄ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1054551161211 ላይ ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት በጽ/ቤቱ የግዢ የስራ ሂደት ቢሮ ድረስ በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN No.) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  5. በአቅራቢዎች ዝርዝር ዉስጥ የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ያላቸዉ፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  7. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ለእያንዳንዱ ጨረታ ማስከበሪያ CPO ብር 50,000.00(ሀምሳ ሺህ ብር) ሲሆን ለጥቃቅን ና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ የትኛዉንም የዋስትና ደብዳቤ የማንቀበል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
  8. ተጫራቾች ሰነዳቸዉን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ለየብቻ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡ ቴክኒካሉን ያለፉት ተወዳዳሪዎች ፋይናንሻላቸዉ ይከፈታል ፡፡
  9. ጨረታዉ የሚከፈተዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛዉ ቀን የስራ ቀን ከሆነ በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚዉ ቀን በ4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም በአዳማ ከተማ ገንዘብ/ፅ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ግዢ ክፍል ዉስጥ ይከፈታል፡፡ እለቱ በዓል ወይም መ/ቤቱ ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተጠቀሰዉ ሰዓት ጨረታዉ ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታዉ አሸናፊ ዕቃዎቹን እስከ አዳማ ከተማ ገንዘብ ፅ/ቤት መጋዘን ድረስ በራሱ ወጪ አጓጉዞ ማቅረብ አለበት፡፡
  11. የጨረታዉ አሸናፊ በጨረታ መመሪያ በተሰጠዉ መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በዉስጥ ማስታወቂያ ና በስልክ እንደተገለፀ በ10 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ አስፈላጊዉን የጨረታ ዉል ከአዳማ ከተማ ገንዘብ ፅ/ቤት ጋር መፈራረም አለበት፡፡ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘዉ ገንዘብ ገቢ ይሆናል፡፡
  12. ማንኛዉም ተጫራች ለዉድድር የሚቀርበዉ ቫት ተጠቃሚ ሲሆን ፣ 7.5 % በክፍያ ጊዜ የሚቀነስ ይሆናል፡፡
  13. መስሪያ ቤቱ ከሚያደርገዉ የግዢ ዉል 20 ፐርሰንት መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል መሆኑን ተጫራቾች መገንዘብ አለበት፡፡
  14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09-73-33-45-15 በስራ ሰዓት ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Adama City Finance Office seeks licensed suppliers to bid for electronic materials for sector offices. Bidders need valid trade license, tax clearance, VAT registration, TIN, and supplier registration. Winner delivers goods to the office warehouse at own cost.
Save Tender