የአነደድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት – የእህል ውጤቶች፣ የምግብ እህሎች፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ የመኪና ዘይትና ቅባት፣ የቢሮ ጥገና፣ የኤክስካቫተር ኪራይና የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎች ግዥ (ሎት 1–7)
የአነደድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የግልጽ ጨረታ
ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019
በአብክመ በምስራቅ ጎጃም ዞን የአነደድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለወረዳ ባለበጀት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት1. . የእህል ምርት ውጤቶች እስከ ሰኔ 30/2019 ዓ/ም የሚቆይ የኮንትራት ውል አቅርቦት፤ ሎት 2 የምግብ እህሎች እስከ ሰኔ 30/2019 ዓ/ም የሚቆይ የኮንትራት ውል አቅርቦት፤ ሎት 3 አትክልትና ፍራፍሬ እስከ ሰኔ 30/2019 ዓ/ም የሚቆይ የኮንትራት ውል አቅርቦት፤ ሎት 4 የመኪና ዘይትና ቅባት፤ ሎት 5፤የፍትህ ጽ/ቤት የቢሮ ጥገና GC/BC 7 እና በላይ ያላቸውን ሎት 06 የአፈር ግድብ ስራ አገልግሎት የሚውል ኤክስካቫተር ከነደርሶ መልስ ሎቬዱ ኪራይና ናፍጣና ሌሎች ወጭዎችን ተጫራቹ ችሎ ፤ሎት 07 የተለያዩ የመኪና እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል::
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፤የስራ ተቋራጭ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፍያ የምስክር ወረቀትና የንግድ ስራ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የግዥ መጠኑ ከብር 500000.00/አምስት መቶ ሽህ ብር /በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት ከፋይነት/ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና ሌሎች ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው::
- የሚገዛውን እቃ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከመጫረቻ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሎት 01 እስከ ሎት 04 እና ሎት 6ና ሎት 7 ያሉትን ለእያንዳንዱ ሎት ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ ሎት 05 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በመ/ቤታችን የገቢ ደረሰኝ በመሂ 1 ገቢ በማድረግ ሰነዱን መግዛት ይችላል ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ጥቅል ዋጋ ለሎት1.እና ሎት 2በቆይታ ጊዜው የሚገዛውን መጠን ታሳቢ ያደረገ ለእያንዳንዱ 20000.00/ሃያ ሽህ ብር/ ለሎት 3. በቆይታ ጊዜው የሚገዛውን አትክልትና ፍራፍሬ መጠን ታሳቢ ያደረገ 5000.00/ አምስት ሽህ አምስት ብር/፤ ለሎት 4 7500.00/ ሰባት ሽህ አምስት መቶ ብር/፤. ሎት 5 20000.00/ሃያ ሽህ ብር/ ሎት 06 10000.00/አስር ሽህ ብር/ ሎት 7 5000.00/አምስት ሽህ ብር/ ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት በማስያዝ ሰነዱን አያይዞ ማቅረብ አለበት::
- ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታዋጋ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 28 ቀናት ጸንቶ መቆየት አለበት።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ስሙን፤ ፊርማውንና ማህተሙን በማሳረፍ ከሎት 01 እስከ ሎት 04 እንዲሁም ሎት 6 እና ሎት 7 የሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀንና እስከ 11ኛው ቀን 3:30 ድረስ አነደድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ማስገባት ያለበት ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን 3:30 ታሽጎ 4:30 ላይ ይከፈታል:: :: በሎት 05 የሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 20 ተከታታይ ቀንና እስከ 21ኛው ቀን 3:30 ድረስ የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ስሙን፤ ፊርማውንና ማህተሙን በማሳረፍ አነደድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት አለበት:: ጨረታው በ21ኛው ቀን 3:30 ታሽጎ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ መክፈቻ ሰዓቱ ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት ያለው ሲሆን በጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት ያልተገኙ ተወዳዳሪዎች በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ::
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የማብራሪያ/የማሻሻያ ጥያቄን በተመለከተ ከሎት 01 እስከ ሎት 04 እና ሎት 6 እና 7 ያሉት ጨረታው ሊዘጋ 5 ቀናት እስኪቀረው እንዲሁም ለሎት 05 ደግሞ ለመጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ የተወሰነው ጊዜ ሊያበቃ 10 ቀናት እስኪቀረው ድረስ ለሚቀርብ የማሻሻያ ወይም የማብራሪያ ጥያቄ ብቻ ይሆናል::
- አሸናፊው አካል ያሸነፈባቸውን እቃዎች ጠቅላላ ወጭውን በመሸፈን ከሎት 01 እስከ ሎት 03 ድረስ ያሉትን ሎጀስቲክና የሎጀስቲክ ግብዓቶችን ውል ከያዘበት ቀን ጀምሮ እንዲያቀርብ በተጠየቀ በ3 ቀናት ውስጥ አነደድ ወረዳ አምበር ከተማ የሚያቀርብ ሲሆን ለሎት 04 እና ሎት 7 ደግሞ ውል ከያዘበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ15 ቀናት አስተዳደር ፑል ንብረት ክፍል ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት: : በሎት 05 አሸናፊ የሆነው አካል ደግሞ ውል ከያዘበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 60/ስልሳ/ቀናት ውስጥ የቢሮ ጥገና ግንባታውን ጨርሶ ማስረከብ ይኖርበታል:: በሎት 6 አሸናፊ የሆነው አካል ደግሞ ውል ከያዘበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ100 ሰዓት የአፈር ግድብ ስራውን ማጠናቀቅ አለበት ::በአጠቃላይ ለሁሉም ሎቶች ለውል መያዣ የሚፈለጉ ወጭዎችን አሸናፊው አካል የሚሸፍን ሲሆን ግዥ ፈጻሚው መ/ቤት ከሎት 05 ውጪ ላሉት ግዥዎች ቅድሚያ ክፍያ አይሰጥም::በጨረታው ለወጡት ሎቶች ሙያ የሚጠይቁ እቃዎች ደግሞ በሚመለከተው ባለሙያ ተረጋግጠው ገቢ ይሆናል:: ግዥ ፈጻሚው አካል ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን በጨረታው መሰረዝ ምክንያት ለወጣው ወጭ ግዥ ፈጻሚው አካል ተጠያቂ አይሆንም::
- ከሎት 05 ውጭ ላሉት ግዥዎች ውድድሩ የሁሉም ሎቶች በጥቅል ዋጋ ስለሚታይ ተጫራቾች በአንድ ሎት ያሉትን ዝርዝር እቃዎች ሁሉንም ዋጋ መሙላት አለባቸው :: ግዥ ፈጻሚው አካል ካወጣው ስፔስፊኬሽን ውጭ በራሱ ስፔስፊኬሽን የሞላ ተወዳዳሪ ከውድድር ውጭ ይሆናል::መ/ቤቱ በሎት 4፤ሎት 6፤ና በሎት 7 የሚገዛቸውን እቃዎች መጨመር ወይም መቀነስ ቢፈልግ 20% መጨመር ወይም መቀነስ መብት አለው::
- በማንኛውም ግዥ ለእቃዎች ከብር 20,000.00/ሃያ ሽህ በላይ፤ ለአገልግሎት ግዥ ደግሞ 10,000.00/አስር ሽህ ብር /በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች አቅራቢው ከሚፈጸምለት ክፍያ ላይ 3% ቅድመ ግብር/ዊዝ ሆልድ ተቀንሶ የሚቀር ሲሆን በውል አፈጻጸም ወቅት የዋጋ ማስተካከያ ማድረግ አይፈቀድም ::
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አነ/ወ/ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በአካል ወይም በስልክ ቁጥራችን 0913271823 /0946088403/0920120967/0920503640 በመደወል ማግኘት ይችላሉ::
የአነደድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Aneded Woreda Finance Office invites bids for seven lots: grain products, food grains, vegetables and fruits, vehicle oil and lubricants, office maintenance (GC/BC 7+), excavator rental for soil dam work, and various vehicle spare parts. Bidders need a valid trade license, contractor competency certificate, tax clearance, and VAT registration if the purchase exceeds 500,000 birr.
