Tender Detail

Tender Details

  • Company Yiha Real Estate P.L.C (ይሓ ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር)
  • Address አዲስ አበባ ስቴድየም ቤተ ዛታ ሆስፒታል ፊት ለፊት "ይሓ ሲቲ ሴንተር" ህንጻ 2ኛ ፎቅ, Phone: 011-5-58-01-29
  • Website
  • Deadline26 Oct 2026, 3:00 PM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityብር 50,000(ሀምሳ ሺ. ብር) በይሓ ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ሥም ሲፒኦ (CPO)
  • opening dateበዕለቱ ጥቅምት 16/02/2019 በስራ ሰዓት ከቀኑ 9:30 ስዓት ይሆናል::
  • Categories Road And Bridge Construction , Building Construction

ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር በሚዛኒን ወለል የደረጃ መወጣጫ (BRIDGE) ለማሰራት ተጠንቶ በቀረበው ዝርዝር ስራዎችና ማተሪያል መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል::

Yiha Real Estate P.L.C (ይሓ ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር)


ይሓ ሪል እስቴት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
YIHA REAL ESTATE P.L.C

ቁጥር: ይሓ/15865/19

የብርጅ(BRIDGE) ሥራ ለማሰራት የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር በሚዛኒን ወለል የደረጃ መወጣጫ (BRIDGE) ለማሰራት ተጠንቶ በቀረበው ዝርዝር ስራዎችና ማተሪያል መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል:: ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ ተጫራቾች GC 4 እና ከዚያ በላይ ፍቃድ ያላችሁ ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7 /ሰባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ::

በዚሁ መሰረት

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /ሶስት መቶ/ በመክፈል ከፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 07 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ::
  2. ተጫራች የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ ይኖርበታል::
  3. ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000(ሀምሳ ሺ. ብር) በይሓ ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ሥም ሲፒኦ (CPO) በማሰራት ማስያዝ ይኖርበታል::
  4. ተጫራች ከዚህ በፊት በጨረታ የተሳተፈባቸው ድርጅቶች(መ/ቤቶች) የመልካም የሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል::
  5. ተጫራች የሚያቀርበውን የጨረታ ሰነዱ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ለየብቻ ለይቶ በማሸግና በኢንቨሎፑ ላይ የተጫራች ማንነት በመግለፅ ክብ ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይኖርበታል::
  6. ተጫራች ከላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ካላሟላ ከጨረታው የሚሰረዝ ይሆናል::
  7. በጨረታ ማስታወቂያ እና ዶክመንቱ ላይ የተገለፁትን የመወዳደሪያ ነጥቦቹን ያሟሉ ተጫራቾች ብቻ ወደ ፋይናንሻል ግምገማ ያልፋል::
  8. ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት በዕለቱ ጥቅምት 16/02/2019 በስራ ሰዓት ከቀኑ 9:00 ስዓት ይሆናል::
  9. ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በዕለቱ ጥቅምት 16/02/2019 በስራ ሰዓት ከቀኑ 9:30 ስዓት ይሆናል::
  10. ተጫራች በጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በሶስት የስራ ቀናት ውስጥ ከጠቅላ ዋጋ 10% ፐርፎርማንስ ቦንድ በማስያዝ 2ኛ ፎቅ ሰው ሃይል አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ ውል ማሰር ይኖርበታል::
  11. ተጫራች በጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በሶስት የስራ ቀናት ውስጥ ከጠቅላ ዋጋ 10% ፐርፎርማንስ ቦንድ አስይዞ 2ኛ ፎቅ ሰው ሃይል አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ ውል ተዋውሎ ወደ ስራው ካልገባ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ብር 50,000 ወደ ይሓ ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ሒሳብ ቁጥር ገቢ ይሆናል::
  12. ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ መገኘት ይችላሉ::

አድራሻ:- አዲስ አበባ ስቴድየም ቤተ ዛታ ሆስፒታል ፊት ለፊት “ይሓ ሲቲ ሴንተር” ህንፃ 2ኛ ፎቅ ስልክ ቁጥር- የቢሮ 011558012 /0115576954/ ሞባይል - 0922079575

ማሳሰቢያ:- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

✨ messages.ai_summary
Yiha Real Estate invites bids to construct a bridge (elevated walkway) at Mizanin Wolel, per the provided works and materials list. Eligible bidders need GC 4 or higher grade, a renewed business license, TIN and VAT registration, prior good performance records, and separately sealed technical and financial envelopes.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender