Tender Detail

Tender Details

  • Company South Ethiopia Gamo Zone Finance and Plane Development
  • Address , Phone: 0468812558
  • Website
  • Deadline03 Nov 2026, 9:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300(ሦስት መቶ ብር)
  • Bid Security200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት
  • opening dateማስታወቂያው ከወጣበት እስከ 16ኛው ቀን በ3:30 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ 4:00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል::
  • Categories Wood And Wood Working , Forest And Tree Sales

የጋሞ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ የደረሰ የጽድ ዛፍ በቁጥር 3398 በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

South Ethiopia Gamo Zone Finance and Plane Development


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጋሞ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ በዞኑ በአ/ምንጭ ዙሪያ ወረዳ እና በጨንቻ ዙሪያ ወረዳ መሀል በደገና ቀበሌ የጉጫ ኮንፓርትመንት ሰው ሰራሽ ደን 8.09 ሄክታር ላይ ያረፈ የደረሰ የጽድ ዛፍ በቁጥር 3398 በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ::

  1. በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ ያላቸው፣
  3. የንግድ ፍቃድና ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ያላቸው፣
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ከፋይ መሆናቸው ማስረጃ ያላቸው፣
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
  6. ማንኛውም ተጫራቾች ከውድድሩ በፊት የደኑን ማገኛ ቦታ በራሱ ወጪ አይቶ የአንዱን ጽድ ነጠላ ዋጋ መሙላት ይኖርበታል::
  7. ተጫራቾች ደኑን ለማንሳት አስፈላጊውን የሰው ኃይልና መሣሪያዎችን በራሣቸው ማቅረብ የሚችሉ፣
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 15 ባሉት ቀናት ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር/ በጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የባንክ ሂሣብ ቁጥር 1000038613263 በማስገባት እና የባንክ አድቫይስ ይዘው ከጋሞ ዞን ገቢዎች መምሪያ ደረሰኙን በማሳየት ከጋሞ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ::
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (BiD security) 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት በዋናው የሕጋዊነት ሰነድ እንቬሎፕ ውስጥ አስገብተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በማዘጋጀት በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በግዥና ን/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው ሣጥን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን እስከ 3:30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው ከወጣበት እስከ 16ኛው ቀን በ3:30 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ 4:00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል::
  12. የጨረታ መክፈቻ በበዓላት ወይም በሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል::
  13. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  14. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር- 046-881-3338 በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ::

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጋሞ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ
አ/ምንጭ

✨ messages.ai_summary
Gamo Zone Finance and Plan Development seeks to sell 3,398 mature zid trees by tender, located on 8.09 hectares of man-made forest in Dega Kebele, between Amnch and Chencha woredas. Bidders need a valid trade license, tax ID, VAT registration, and must inspect the site and submit a unit price.
Save Tender