ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በኤሌክትሪክ የሚሰራ የእቃ ማጓጓዣ ጋሪ (Electric Pallet Truck) እና የወረቀት መፍጫ ማሽን (Paper Shredder) በድጋሚ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
Berhanena selam printing enterprise (ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 025/19
ድርጅታችን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በድጋሚ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- በጨረታ አንድ (ሎት 1)፡- እስከ 1,500 ኪ.ግ የመጫን አቅም ያለው በኤሌክትሪክ የሚሰራ የእቃ ማጓጓዣ ጋሪ (Electric Pallet Truck) ብዛት 2 ግዥ፣
- በጨረታ ሁለት (ሎት 2) የወረቀት መፍጫ ማሽን (Paper Shredder) ብዛት 1 ግዥ፤
በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት የፈልጋል። ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት (አራት ኪሎ) አዲሱ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 500.00 ከፍለው በመግዛት የፋይናንሺያል እና የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ተጫራቾቹ ለጨረታ ማስከበሪያ 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው። ጨረታው 10/3/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች፣ የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ሕንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል። የፋይናንሺያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
ስልክ ቁጥር፡-011-1-55-52-30
ድረ ገጽ (www.ethbspe.org)
Berhanena selam printing enterprise
አዲስ አበባ
