Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251 46 221 2789
  • Websitehttps://dbe.com.et/
  • Deadline26 Nov 2026, 9:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/5ኛ (20%) ብር16,841,176.65/ አስራ ስድስት ሚሊዮን ስምንት መቶ አርባ አንድ ሺ አንድ መቶ ሰባ ስድስት ብር ከ65/100 ሳንቲም/
  • opening dateኅዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጧቱ 4:00 እስከ 6:00 ሰዓት
  • Categories Machinery , Sales, Disposals And Foreclosure , Business, Industry And Factory Foreclosure

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ከአቶ ብሩህ ተስፋ ጥሩነህ ባልተከፈለ ዕዳ ምክንያት በአዋጅ ቁጥር103/1990 እና 807/2005 መሰረት የተረከባቸውንና ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለጹትን ለቡና መቁላት፣ መፍጨትና ማሸግ ስራ የሚያገለግሉና ጣሊያን ስሪት የሆኑ ማሽነሪዎችና መሳሪያዎች ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታለመሸጥ/ለማከራየት ይፈልጋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት


የዝግ ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ከአቶ ብሩህ ተስፋ ጥሩነህ ባልተከፈለ ዕዳ ምክንያት በአዋጅ ቁጥር103/1990 እና 807/2005 መሰረት የተረከባቸውንና ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለጹትን ለቡና መቁላት፣ መፍጨትና ማሸግ ስራ የሚያገለግሉና ጣሊያን ስሪት የሆኑ ማሽነሪዎችና መሳሪያዎች ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታለመሸጥ/ለማከራየት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ.የንብረቱ ዝርዝርብዛት በቁጥርየጨረታው መነሻ ዋጋየንብረቱ ሁኔታሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት
1.Coffee Roasting and Grinding Machinery84,205,883.24አዲስህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4:00 እስከ 6:00 ሰዓት
1.1Pneumatic Loader Model - ELP601
1.2Coffee Roaster Model – TTG 601
1.3Roasted Coffee Receiving Hopper1
1.4Loader (Pneumatic Conveyor system1
1.5Suction Pump group for Pneumatic conveyor system1
1.6Silos for roasted coffee beans2
1.7Drop diverter valve2
1.8Additional Unit of Pneumatic conveyor to feed the roasted coffee beans to packing machine1
1.9Coffee Grinder Model-MAIN 3001
1.10Raking Screw Conveyor to feed the ground coffee to silo1
1.11Ground Coffee Silo1
1.12Electric Control Panel1
2.Auto Weighing and Vertical Packaging Machinery
- Brand: DOLZAN, Model: D150-C1,Origin:Italy,Manufacturing Year : 2021
1

የዝግ ጨረታው መመሪያ:

  1. በዝግ ጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ስምና አድራሻውን እንዲሁም ንብረቱን የሚገዛበትን ዋጋ የሚገልጽ ማመልከቻ ፣የታደሰ መታወቂያ ኮፒ፣የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/5ኛ (20%) ብር16,841,176.65/ አስራ ስድስት ሚሊዮን ስምንት መቶ አርባ አንድ ሺ አንድ መቶ ሰባ ስድስት ብር ከ65/100 ሳንቲም/ የያዘ በኢ/ት ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ስም የተዘጋጀና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አያይዞ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በኢ/ት ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም. ጠዋት 3:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላል፡፡
  2. ንብረቱ በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ይርጋለም ከተማ፣ ይርጋለም አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሼድ ውስጥ ይገኛል፡፡
  3. የሚሸጠው ንብረት የገባው ከቀረጥ ነጻ ሲሆን ገዥው የቀረጥ ነጻ መብት ተጠቃሚ እንዲሆን ባንኩ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ ፈቃዱን ካላገኘ ግን የቀረጥ ክፍያው በገዥው ይፈጸማል፡፡
  4. ንብረቶቹን ሙሉ በሙሉ በካሽ/ በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች የንብረቱ የሽያጭ ዋጋ ላይ 15% ተእታ (VAT) እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ የታክስ ክፍያዎችን ጨምሮ ይከፍላል፡፡
  5. የጨረታው አሸናፊ ባንኩ ማሸነፉን በደብዳቤ ከገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መከፈል ይኖርበታል፡፡ የጨረታው አሸናፊ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው በድጋሚ ይካሄዳል፡፡ ለተሸነፉ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
  6. ተጫራቹ በከፊል ዱቤ ለመከራየት አሸናፊ ከሆነ ባንኩ ማሸነፉን እንዲያውቅ ካደረገበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ውስጥ የባንኩን የማሽነሪ ኪራይ መስፈርት በማሟላት እና የሚጠበቅበትን ቀሪ ክፍያ አጠቃሎ በመክፈል የማሽነሪ ኪራይ ውል መፈረም ይኖርበታል፡፡በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፡፡
  7. የካፒታል ዕቃውን ካለበት ይርጋለም አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሼድ ወደ ሚፈልግበት ቦታ የማጓጓዣ ወጪ፣የጉዞ ኢንሹራንስ፣የመትከያ፣ስራ የማስጀመሪያና ተያያዥ ወጪዎችን ገዥው/ ተከራይ ይሸፍናል፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኅዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጧቱ 4:00 እስከ 6:00 ሰዓት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ይካሄዳል።
  9. ስለ ንብረቱ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ሎን ዎርክአውት ዲቭዥን በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር +251 46 221 2789 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡
  10. ንብረቱን ለመጎብኘት ከሀዋሳ ዲስትሪክት ሎን ዎርክአውት ዲቭዥን ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይቻላል፡፡
  11. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት

✨ messages.ai_summary
Ethiopia's Development Bank (Hawassa District) is selling by closed tender Italian-made coffee roasting, grinding and packing machinery and equipment, including a roaster, grinders, pneumatic conveyors, silos and a DOLZAN packaging machine, located in Yirgalem Agro Industry Park. Bidders must submit a CPO; full cash payment plus VAT applies.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender