Tender Detail

Tender Details

  • Company Dire Dawa Customs Branch Office (ድሬዳዋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)
  • Address ድሬዳዋ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0251-12-49-28
  • Website
  • Deadline06 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 100 (በአክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን)
  • Bid Securityለእያንዳንዱ ምድብ የዋጋው 5% (CPO)
  • opening date27/02/2019 4:00
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግልጽ ጨረታ ባለበት ሁኔታ ኦላይን ለመዳድር ለመሸጥ ይፈልጋል።

Dire Dawa Customs Branch Office (ድሬዳዋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)


የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
ኦላይን የግልጽ ጨረታ ቁጥር AE02/2019

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግልጽ ጨረታ ባለበት ሁኔታ ኦላይን ለመዳድር ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በግልጽ ጨረታ ቁጥር AE02/2019 በ27/02/2019 የተለያዩ ሞባይል ቀፎዎች፣ አስፎርፖርት፣ ጫማ፣ የግንባታ እቃ፣ ቴሌቪዥን እና የተለያዩ ዕቃዎች ባሉበት በኦላይን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች

  1. በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑ ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሠጠ ማስረጃ እና መለያ ቁጥሩን ጨምሮ በአክሽን ኢትዮጵያ ኦላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
  2. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች የሚገኙት በድሬዳዋ ሙድአነኖ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የውርስ ዕቃ መጋዘን ውስጥ ነው።
  3. በግልጽ ጨረታው ላይ በመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተጠቀሰው ቀን መሰረት 100 ብር በመክፈል ከአክሽን ኢትዮጵያ ኦላይን መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ እና የዕቃዎቹን ሳንፕል ማግኘት ይችላሉ። እቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
  4. ጨረታው የሚካሄደው ሙሉ ለሙሉ በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ነው።
  5. በግልጽ ጨረታ በሽያጭ የቀረቡት እቃዎች በኮድ የተከፋፈለ ሲሆን ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት።
  6. በግልፅ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ምድብ የሰጡት ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሰከረለት (CPO) (CUSTOMS COMMSSON DREDAWA BRANCH OFECE) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ በማሰራት ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ በአካል ወደ አክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦላይን አክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች ግልጽ ጨረታ ኦላይን ከሆነበት ከ20/02/2019 4፡00 ጀምሮ እስከ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን 27/02/2019 4፡00 መሳተፍ ይጠበቅባቸዋል።
  8. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች በጨረታ ዋስትና ያስያዙት ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ይሆናል።
  9. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን ዕቃዎች አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል።
  10. ከላይ በተራ ቁጥር 9 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ዕቃውን ያልተረከበ ተጫራች በጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒ ለባለስልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።
  11. የጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን በማግኘት በስልክ መስመር 05-11-5511 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
በተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0915460970 ( 0912885746) መደወል ይቻላል

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Dire Dawa Customs Branch Office is selling assorted inherited goods held in its warehouse—mobile phone cases, sportswear, shoes, construction materials, televisions and other items—via online public auction. Bidders need a renewed trade licence relevant to the goods, VAT registration, and current tax payment proof.
Save Tender