በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ/ፈ/ማ/ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳ 04 ለሚያሰራቸው የግንባታ ስራዎች በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማ/ጽ/ቤት
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:2/2019
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ/ፈ/ማ/ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳ 04 ለሚያሰራቸው የግንባታ ስራዎች በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የተሟላ የሰው ሀይል እና ማሽነሪዎች በማቅረብ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ስራውን ማጠናቀቅ የሚችል የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
| ሎት | የፕሮጀክት ስም | ወረዳ | የጨረታ ዋስትና ብር መጠን | የተቋራጭ ደረጃ | ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ | አድራሻ |
| 1 | ጀሞ 1 ደረጃ ት/ቤት ጥበቃ ማማ | 04 | 2% | ደረጃ 5 እና 6 ብቻ | 90 ቀን | ቤተል ፖስታ ቤት አካባቢ |
| 2 | ድሬኔጅ ስራ | 04 | 2% | ደረጃ 7 እና 8 ብቻ | 90 ቀን | ✓ |
- ለስራው ንግድ ምዝገባና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የ2018 ዓ.ም የከፈሉ፣ የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን እንዲሁም በ2018 በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ከሊራንስ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ያላቸው (supplier list)፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።
- ተጫራቾች የጨረታው ውድድር ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ግምገማ ስለሚኖረው ቴክኒካል አንድ ኦርጂናል አንድ ኮፒ እና ፋይናንሺያል አንድ ኦርጂናል አንድ ኮፒ በማሸግ በድምሩ አራት ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ፎርማ፣ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም በመጻፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም (BID BOND or BID SECURITY) ለብቻ በታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ፊርማ እና ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባችኋል። በተጨማሪም የታሸገውን 2 ፖስታ የፋይናንሻል እንዲሁም ቴክኒካል ሰነድ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም፣ፊርማ እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይንም ሙሉ በሙሉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት (work Days) ቅዳሜን ጨምሮ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ ዘወትር ከጠዋቱ 2:30 እስከ 10:30 ድረስ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 4ኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 402 ህ/ተ/በጎ/ፈ/ማ/ጽ/ቤት መሰረተ ልማት በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱት ማስረጃዎች ዋናው (Original) እና የማይመለስ ቅጂ (copy) ይዞ በመቅረብ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው የስራ ቀን (work Days) ጠዋት 4:00 ሰዓት ድረስ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ/ፈ/ማ/ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ማሳሰቢያ ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ያለው 16 ኛው የስራ ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣዩ የስራ ቀን 4:00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ እለት 4:30 ላይ የሚከፈት ይሆናል። - ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡት ዋጋ ወቅታዊ የገበያ ዋጋን ያላገናዘበ እጅግ የተጋነነ ዝቅተኛ ወይም ከፍተኛ የሚሰራውን ሥራ ያላማከለ ከሆነ ተጫራቹ የዋጋ ትንታኔ (Cost Break down) ከተገቢው መረጃ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል። ሆኖም የቀረበው ዋጋ ከሥራው ጋር ያልተመጣጠነ (unbalanced rate) ከሆነ ተጫራቹ ከጨረታ ውድድሩ ውጪ ይደረጋል።
- ተጫራቹ ለጨረታ ያስገባው ፋይናንሻል ሰነድ ነጠላ ዋጋ ላይ ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ (Unsigned Rate Correction) እና ነጠላ ዋጋው ላይ ፍሉድ መጠቀም (to use fluid for Rate Correction) ከጨረታ ተወዳዳሪነት ያሰርዛል።
- በስራ ዝርዝር ላይ ነጠላ ዋጋ አለመሙላት (unfilled rate) ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል።
- እጃቸው ላይ ምንም አይነት ስራ እንደሌላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ ስራም ካላቸው 75% መድረሱን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ። ጨረታ መሳተፍ የሚቻለው በአንድ ሎት ብቻ ነው።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-
የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 4ኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 402 ህ/ተ/በጎ/ፈ/ማ/ጽ/ቤት መሰረተ ልማት ቡድን በጽሑፍ ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ።
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ/ፈ/ማ/ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Kolfe Keranio Sub-City is tendering construction works in Woreda 04 under two lots: Lot 1, a guard tower for Jemo 1 Primary School (Grade 5 and 6 contractors only), and Lot 2, drainage works (Grade 7 and 8 contractors only). Bidders must hold valid trade registration and business license, tax compliance for 2018 E.C., renewed 2018 E.C. business license, competency registration certificate from the Addis Ababa Construction Permit and Control Authority, and a 2018 E.C. tender participation clearance from the relevant body. They must also be on the supplier list, VAT-registered with a TIN, and submit technical and financial documents in original and copy, each sealed separately with the company's signature, stamp, and project name. Bidders may participate in only one lot and must show they have no ongoing works, or that any existing works are at least 75% complete. Unbalanced or unrealistic prices may lead to disqualification, and missing unit rates will be treated as free work. The office reserves the right to cancel the tender in whole or in part.
