ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የውሃ ጉድጓድ ጠላቂ ፓምፕግዥ እና ተከላ ግልፅ ጨረታ Electric submersible pump
ጣና ፍሎራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የውሃ ጉድጓድ ጠላቂ ፓምፕግዥ እና ተከላ ግልፅ ጨረታ
Electric submersible pump
ኩባንያችን ጣና ፍሎራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአማራ ክልል በባህርዳር ዙሪያ ወረዳ በ124 ሄክታር ላይ በአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት የተሰማራ ኩባንያ ሲሆን ለእርሻ ልማቱ አገልግሎት የሚውል ሁለት የውሃ ጉድጓድ ጠላቂ ኤሌክትሪክ ሰመር ሰብል ፓምፕ፣ ኤሌክትሪክ ቦርድ፣ኬብል፣ ፓይፕ እና ፊቲንግ እንዲሁም ተያያዥ እቃዎችን ግዥና ተከላ በጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ የፓምፑን አጠቃላይ ስፔሲፊኬሽን በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፣
የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ኩባንያው ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- ህጋዊ የኤሌክትሮ መካኒካል ንግድ ፈቃድ ያለው እና በደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ ተቋራጭ የሆነ
- የኤሌክትሮ መካኒካል የድርጅቱን የብቃት ሰርተፊኬት ማያያዝ የሚችል
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- የተ. እ .ታ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-6 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- "ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያውን ሲፒኦ በጣና ፍሎራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም በተሰራ ሲፒኦ ለማጫረትበት ግዥ ከተቀመጠው የመጫረቻ ዋጋ 2% ፐርሰንት ማስያዝ ይኖርበታል ፡
- የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ (ቅጹን) የማይመለስ ብር 500 በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 004 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ጣና ፍሎራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ በመገኘት የዋጋ ማቅረቢያ ቅጹን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ከወጣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ታሽጎ በባህር ዳር ጣና ፍሎራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0918481598/0913696383 ወይም 0582204798 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞሉ የዋጋና የሞዴል መረጃዎችን የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉ ተከታታይ 5 ቀናት ውስጥ ባህር ዳር ጣና ፍሎራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ ድረስ በመቅረብ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-6 የተገለፁትን ማስረጃዎች አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ኩባንያው ውሉን እንደየአስፈላጊነቱ በየስድስት ወሩ ሊያድስ ይችላል፡፡ ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡-የዋና መስሪያ ቤት አድራሻ፡ ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 13 ሀይሌ ት/ቤት ጎን፣ ስልክ ቁጥር 0582204798 ኢሜል፡ tanaflorapum@gmail.com, tanafloragm@gmail.com
ጣና ፍሎራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
✨ messages.ai_summary
Tana Flora invites bids for supplying and installing two electric submersible pumps for its 124-hectare farm in Bahir Dar Zuria, including electrical board, cable, pipes and fittings. Bidders need a valid electromechanical trade licence, Grade 3+ contractor status, TIN and tax clearance.
