ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር በሚዛኒን ወለል የደረጃ መወጣጫ (BRIDGE) ለማሰራት ተጠንቶ በቀረበው ዝርዝር ስራዎችና ማተሪያል መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
YIHA REAL ESTATE P.L.C
ቁጥር፡ ይሓ/15865/19
ቀን፡ 05/02/2019
የብርጅ(BRIDGE) ሥራ ለማሰራት የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር በሚዛኒን ወለል የደረጃ መወጣጫ (BRIDGE) ለማሰራት ተጠንቶ በቀረበው ዝርዝር ስራዎችና ማተሪያል መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ ተጫራቾች GC 4 እና ከዚያ በላይ ፍቃድ ያላችሁ ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7 /ሰባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
በዚሁ መሰረት
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /ሶስት መቶ/ በመክፈል ከፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 07 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራች የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000(ሀምሳ ሺ ብር) በይሓ ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ሥም ሲፒኦ (CPO) በማሰራት ማስያዝ ይኖርበታል።
- ተጫራች ከዚህ በፊት በጨረታ የተሳተፈባቸው ድርጅቶች(መ/ቤቶች) የመልካም የሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራች የሚያቀርበውን የጨረታ ሰነዱ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ለየብቻ ለይቶ በማሸግና በኢንቨሎፑ ላይ የተጫራች ማንነት በመግለፅ ክብ ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራች ከላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ካላሟላ ከጨረታው የሚሰረዝ ይሆናል፡፡
- በጨረታ ማስታወቂያ እና ዶክመንቱ ላይ የተገለፁትን የመወዳደሪያ ነጥቦቹን ያሟሉ ተጫራቾች ብቻ ወደ ፋይናንሻል ግምገማ ያልፋል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት በዕለቱ ጥቅምት 16/02/2019 በስራ ሰዓት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ይሆናል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በዕለቱ ጥቅምት 16/02/2019 በስራ ሰዓት ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ይሆናል።
- ተጫራች በጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በሶስት የስራ ቀናት ውስጥ ከጠቅላ ዋጋ 10% ፐርፎርማንስ ቦንድ በማስያዝ 2ኛ ፎቅ ሰው ሃይል አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ ውል ማሰር ይኖርበታል፡፡
- ተጫራች በጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በሶስት የስራ ቀናት ውስጥ ከጠቅላ ዋጋ 10% ፐርፎርማንስ ቦንድ አስይዞ 2ኛ ፎቅ ሰው ሃይል አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ ውል ተዋውሎ ወደ ስራው ካልገባ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ብር 50,000 ወደ ይሓ ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ሒሳብ ቁጥር ገቢ ይሆናል፡፡
- ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ መገኘት ይችላሉ።
አድራሻ፡– አዲስ አበባ ስቴድየም ቤተ ዛታ ሆስፒታል ፊት ለፊት ‹‹ይሓ ሲቲ ሴንተር›› ህንጻ 2ኛ ፎቅ ስልክ ቁጥር-
የቢሮ 011558012 /0115576954/ ሞባይል – 0922079575
ማሳሰቢያ፡– ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
