ፀደይ ባንክ አ.ማ ከስር የተዘረዘሩትን ዕቃዎች/ስራዎች/አገልግሎቶች ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ማሰራት ይፈልጋል፡፡
Tsedey Bank S.C. (ፀደይ ባንክ አ.ማ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/007/2019
ፀደይ ባንክ አ.ማ ከስር የተዘረዘሩትን ዕቃዎች/ስራዎች/አገልግሎቶች ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ማሰራት ይፈልጋል፡፡
| ሎት-1 | ኮምፒውተር (Desktop computer) | Cori 3 ብዛት | 1,519 |
| Cori 5 ብዛት | 292 | ||
| ሎት-2 | የህንፃ እድሳት በስምንት ዲስትሪክቶች ለሚገኙ ህንፃዎች እና ባህርዳር ለሚገኘው ዋና መ/ቤት BC / GC -7 and above | ||
| ሎት-3 | የደንብ ልብስ | የአደጋ መከላከያ ጫማ (Safety Shoe) | 10 |
| የእግር ሹራብ | 8,299 | ||
| ካራቫት | 7,012 | ||
| ቀብ | 6,632 | ||
| ሻሽ | 1,308 | ||
| ሸርጥ | 841 | ||
| ጃንጥላ | 610 | ||
| የእጅ ጓንት ፕላስቲክ | 648 | ||
| ካኪ የስራ ካፖርት | 697 | ||
| የዝናብ ልብስ | 3,130 |
ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ድርጅት/ነጋዴ/ መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ # የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት # በጨረታ ለመካፈል/ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት/ክሊራንስ ጊዜው ያላለፈበት፡፡ ቴክኒካል ዶክመንትና የሚያቀርቡበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ የአጠቃላይ ዋጋውን 2% ወይም የአጠቃላይ ዋጋው 2% ከብር 500,000.00 የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000.00 በሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የ90 ቀን በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡ ከየትኛውም የፀደይ ባንክ አ.ማ ቅርንጫፍ የተሰጠ ሲፒኦም ሆነ ባንክ ጋራንቲ ተቀባይነት የለውም፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከጥቅምት 09 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ አምስት መቶ ብር /500.00/ ፀደይ ባንክ ለገሃር ቅርንጫፍ ወይም በማንኛውም የፀደይ ባንክ ቅርንጫፍ በመክፈል ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ከግዥ ክፍል ሰነዱን መዉሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ ጨረታው እስከሚዘጋበት ድረስ፡ ሎት-1 ጥቅምት 23 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ድረስ፣ ሎት-2 ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ድረስ እንዲሁም ሎት -3 ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ ጤና ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት 16ተኛ ፎቅ ግዥና ዉል አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በተዘጋበት ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የጨረታዉ መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛዉም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ ጤና ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ በሚገኘው የፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት ስልክ ቁጥር 0115581658
ፀደይ ባንክ አ.ማ
✨ messages.ai_summary
Tsedey Bank seeks licensed bidders for three lots: desktop computers (Core 3 and Core 5), building renovation for eight district offices and its Bahir Dar head office (BC/GC-7 and above), and staff uniforms including safety shoes, socks, ties, belts, shirts, umbrellas, gloves, work coats and raincoats.
