Tender Detail

Tender Details

  • Company Hibret Bank S.C (ሕብረት ባንክ አ.ማ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251114655222
  • Websitehttps://www.hibretbank.com.et/
  • Deadline26 Oct 2026, 4:00 PM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Priceብር 500.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityየአንድ ወር ኪራይ 25% (CPO)
  • opening dateጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

ሕብረት ባንክ አ.ማ. አዲስ አበባ ከተማ፣ በልደታ ክ/ከተማ፣ በወረዳ 7 ሰንጋ ተራ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የዋናው መስሪያ ቤት ሕብር ሕንፃ ብሎክ "ቢ" ላይ የሚገኘውን ዘጠነኛ /9ኛ/ ወለል እንዲሁም ብሎክ "ኤ" ከአንደኛ እስከ ሰስተኛ ወለል ላይ የሚገኙትንና የተለያዩ ስፋት ያላቸውን አስራ አንድ/11/ ክፍሎች ለቢሮ አገልግሎት እንዲውሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

Hibret Bank S.C (ሕብረት ባንክ አ.ማ)


የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፡ ሕባ/002/2019

ሕብረት ባንክ አ.ማ. አዲስ አበባ ከተማ፣ በልደታ ክ/ከተማ፣ በወረዳ 7 ሰንጋ ተራ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የዋናው መስሪያ ቤት ሕብር ሕንፃ ብሎክ "ቢ" ላይ የሚገኘውን ዘጠነኛ /9ኛ/ ወለል እንዲሁም ብሎክ "ኤ" ከአንደኛ እስከ ሰስተኛ ወለል ላይ የሚገኙትንና የተለያዩ ስፋት ያላቸውን አስራ አንድ/11/ ክፍሎች ለቢሮ አገልግሎት እንዲውሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ኪራይ ፈላጊዎች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት የጨረታ ሰነዱን በመግዛት የመጫረቻ ሰነድ ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች ይህ ጨረታ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋዜጣ ከወጣ ከ2 ቀናት በኋላ ማለትም ከጥቅምት 04 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም. የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በአቅራቢያ በሚገኙ የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር IN0403007 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ ሰነዱን በልደታ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 7 ሰንጋ ተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ 19ኛ ወለል በግዥ እና ኮንትራት አስተዳደር መምሪያ በመገኘት መግዛት ይቻላል፡፡
  3. ለጨረታ የቀረበውን ወለል ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ማለትም ከጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም. ውስጥ ሰኞ፣ ዕሮብ እና አርብ ከጠዋቱ 3:00 - 10:00 ሰዓት በባንኩ ዋና መ/ቤት በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሞልተው ከማስገባታቸው በፊት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተካተተውን የተጫራቾች መመሪያ በደንብ ማየት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለጨረታ የቀረበውን ይዞታ ቢከራዩ የሚከፍሉትን የአንድ ወር ኪራይ አንድ አራተኛ (25%) በባንክ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) የጨረታ ሰነዱን ሲያቀርቡ ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን የዋስትናው የአገልግሎት ጊዜውም /Validity Date/ ዘጠና (90) ቀናት ይሆናል፤
  6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያስይዙትን የባንክ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) የሚያሰሩት ከሕብረት ባንክ ውጪ በሆኑ በማንኛውም ባንኮች መሆን አለበት፡፡
  7. እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት፡፡
  8. ተጫራቾች ለጨረታው አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን በማሟላት ልደታ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 7፣ ሰንጋ ተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ 19ኛ ፎቅ በግዥ እና ኮንትራት አስተዳደር መምሪያ በሚገኝ የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ጥቅምት 12፣13፣14 እና 16 ቀን 2019 ዓ.ም. እስከ ቀኑ 10:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  9. ጨረታው ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ባንኩ ዋና መስሪያ ቤት አራተኛ /4ኛ/ ወለል ላይ በሚገኘው አዳራሽ ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  10. በጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው የተጫራቾች መመሪያ መሠረት ያልቀረበ የመጫረቻ ሰነድ/ተጫራች ከውድድር ሊሰረዝ ይችላል፡፡
  11. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011- 470 41 72 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!!

✨ messages.ai_summary
Hibret Bank invites bids to rent office space: the 9th floor of Block B and eleven rooms of varying sizes on floors 1–6 of Block A at its new headquarters in Addis Ababa. Bidders must follow the bid document instructions; non-compliant bids may be rejected.
Save Tender