በጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተማ መሰረተ ልማት መምሪያ በ2019 ዓ.ም የን/ከ/አስ/አካ/ፕ/ፅ/ው/አረ/ል/ጽ/ቤት ለከተማው ውስጥ የተከሰቱ ችግኞችና አሳሮችን ውሃ ለማጠጣት እና የከተማውን የላንድፊል/የደረቅ ቆሻሻ ቦታ ለማስደልደል ስለተፈለገ በተያዘው እቅድ መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ
የአገልግሎት ግዥ ብሄራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተማ መሰረተ ልማት መምሪያ በ2019 ዓ.ም የን/ከ/አስ/አካ/ፕ/ፅ/ው/አረ/ል/ጽ/ቤት ለከተማው ውስጥ የተከሰቱ ችግኞችና አሳሮችን ውሃ ለማጠጣት እና የከተማውን የላንድፊል/የደረቅ ቆሻሻ ቦታ ለማስደልደል ስለተፈለገ በተያዘው እቅድ መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መምሪያው የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይገልፃል፡፡
ሎት 1 የውሃ ማጠጫ ቦቴ ኪራይ
ሎት 2 ዶዘር ኪራይ
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በራሳቸው በኩል የቀረቡ ለመሆናቸው በፊርማ እና በድርጅቱ ማህተም በማረጋገጥ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚሰሩ ስራዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /እስፔሲፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ቡድን ገንዘብ ቤት የቢሮ ቁ 21 ከ06/02/2019 እስከ 15/02/2019 ዓ.ም ማግኘት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ጨረታው ከሚከፈትበት ጊዜ ጀምሮ ለ30 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ከሚከፈትበት ጊዜ ጀምሮ ለ60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድቦንድ/ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 50,000 /ሃምሳ ሺ/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለበት ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች ለምዘና የሚያገለግል መሰረታዊ ሰነድ /የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት እና ሌሎችን/ እና ፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ አዳራሹ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 15/02/2019 ዓ.ም 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በቀን 16/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በ16/02/2019 ዓ.ም በ4:30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ሆኖም ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለተሳተፉበት ላወጡት ወጭ መምሪያው ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች/ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 23 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0918712038 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጎንደር ከተማ አስ/ከ/መ/ል/መምሪያ
✨ messages.ai_summary
Gondar City Infrastructure Directorate seeks bidders to water seedlings and trees within the city and to clear the city's landfill/dry waste site. Lots: water tanker rental and dozer rental. Bidders need a valid trade license, TIN, and VAT registration certificate.
