Tender Detail

Tender Details

  • Company South Ethiopia Regional State Roads Authority (የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን)
  • Address ዲላ ከተማ : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0916866262
  • Website
  • Deadline02 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 400.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 25,000.00 (CPO ወይም የባንክ ዋስትና)
  • opening dateበዚያኑ ቀን ከቀኑ 8:30
  • Categories Audio Visual, Photography And Filming Service And Equipment , Camera

የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የቪዲዮ እና የፎቶ ማለትም 'DUAL' የሆነ ካሜራ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

South Ethiopia Regional State Roads Authority (የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን)


የቪዲዮ እና ካሜራ ግዥ ለመፈፀም የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ደኢመባ ቁጥር 03/2019

የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የቪዲዮ እና የፎቶ ማለትም 'DUAL' የሆነ ካሜራ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፡-

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ላላቸው ግዢዎች የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ፣ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆናቸው የምዝገባ ማስረጃ እና በጨረታ ለመሳተፍ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳብ የሚያቀርቡበትን የጨረታ ሰነድ የቴክኒክ እና ፋይናንሻሉን አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ የጨረታ ማስከበሪያው ደግሞ ኦሪጅናልና ኮፒ በተለየ ፖስታ በማድረግ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፤ አድራሻቸውንና የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት በትክክል ማስፈር አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከባለስልጣኑ ዋና ቢሮ ቁጥር --- መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  5. ተጫራቾች በእንግሊዘኛ የተጻፈውን የቴክኒክ ዝርዝር መግለጫ በሚጠይቀው መሠረት መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህንን ያልሞሉት የቴክኒክ ዝርዝር መግለጫ እንዳልቀረበ ተቆጥሮ የማቅረቢያ ሰነዱ ውድቅ ይደረጋል፡፡
  6. ተጫራቾች ከዚህ በታች በቀረበው መሠረት፡-
    ተ.ቁ የዕቃው ዓይነት Qty የጨረታ ማስከበሪያ
    1 DUAL CAMERA 01 25,000.00
    የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ/ሲፒኦ/ ወይም በባንክ ዋስትና ወይም ከኢንሹራንስ ዋስትና በቀር በግዥ መመሪያው ላይ ባሉ አማራጮች በፈለጉት ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም፡፡
  8. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ይሰረዛሉ፡፡ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ይወረሳሉ፡፡ ለወደፊቱም መ/ቤቱ በሚያወጣው ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋል፡፡
  9. ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለ45 ቀናት ፀንቶ መቆየት አለበት፡፡
  10. ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ድርጅት መሆኑ ከተገለፀለት አምስት /5/ ቀናት ውስጥ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና /Performance Bond/ 10% በባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ በማቅረብ ውል መፈረም ይኖርበታል፤ በተጠቀሰው ጊዜ ውል ለመፈረም ፈቃደኛ ያልሆነ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ማስከበሪያ ይወረሳል፡፡

ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም
የስልክ ቁጥር 0461315012/0923690085/0911041...
ዲላ ኢትዮጵያ

የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን

✨ messages.ai_summary
South Ethiopia Regional State Roads Authority seeks bids to supply one dual video/photo camera. Bidders must hold a valid business or service license, VAT registration, supplier registration, and a supporting letter from the relevant government body. Technical specifications in English must be completed or the offer is rejected.
Save Tender