የፅህፈት፣ ህትመት፣ ጎማ፣ የፅዳት፣ ቋሚ፣ ኤሌክትሪክ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ መድሀኒት፣ ደንብ ልብስ፣ የእስረኛ ቀለብና የተለያዩ አገልግሎቶች ግዥ (18 ሎቶች, 001/2019) - የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር አቃ/ቃ/ክ/ከ/ፖ/መምሪያ 001/2019 ዓ/ም
አቃ/ቃ/ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ በ2019 በጀት አመት ለመምሪያው የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች ፣የተለያዩ ህትመት ውጤቶች፣ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች ፣የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች፣ የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች፣ የተለያዩ የኤሌክትሪክና የምህንድስና ዕቃዎች፣ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችና ጥገና፣ የፎቶ ኮፒ፣ የኮምፒውተር ፣የፕሪንተር ጥገና ሰርቪስ እና ፎርማት፣ የተለያዩ የህክምና መድሀኒት፣ ሪጀንት እና የላብራቶሪ መሳሪያዎች፣ የተለያዩ የደንብ ልብሶች ፣የሽንት ቤት መምጠጫ መኪና ኪራይ ፣የእስረኛ ቀለብ፣ የክሬን አገልግሎት ፣የሆቴል መስተንግዶ፣ የዊል ቫላንስ የመሳሰሉትን ስራዎች የሚሰራ ጋሚስታ፣ ሰርቪስ የሚሰጥ የመኪና ኪራይ ፣የተለያዩ እቃዎችን የሚጭን የመኪና ኪራይ ፣የትርጉም ስራ ፣መኪና ላቢያጅ፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ ሲሆን፡-
| ሎት | የጨረታ ዓይነት | የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን |
| 01 | የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች | የጠቅላላው እቃ 2% |
| 02 | የተለያዩ ህትመት ውጤቶች | >> |
| 03 | የተለያዩ የመኪና ጎማዎች | >> |
| 04 | የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች | >> |
| 05 | የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች | >> |
| 06 | የኤሌክትሪክና የምህንድስና ዕቃዎች | >> |
| 07 | የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችና ጥገና የፎቶ ኮፒ፣ የኮምፒውተር ፣የፕሪንተር ጥገና ሰርቪስ | >> |
| 08 | የተለያዩ የህክምና መድሀኒት፣ሪጀንት እና የላብራቶሪ መሳሪያዎች | >> |
| 09 | የተለያዩ የደንብ ልብሶች | >> |
| 10 | የሽንት ቤት መምጠጫ መኪና ኪራይ | >> |
| 11 | የእስረኛ ቀለብ | >> |
| 12 | የክሬን አገልግሎት | >> |
| 13 | የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት | >> |
| 14 | የዊል ቫላንስ የመሳሰሉትን ስራዎች የሚሰራ ጋሚስታ | >> |
| 15 | ሰርቪስ የሚሰጥ የመኪና ኪራይ | >> |
| 16 | የተለያዩ እቃዎችን የሚጭን የመኪና ኪራይ | >> |
| 17 | የትርጉም ስራ | >> |
| 18 | መኪና ላቢያጅ | >> |
ስለዚህ፡- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውቸው መሆን እና በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው ይመለከቱ የሚል ፅሁፍ በግልፅ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፈቃድ መቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የታደሠ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፤
- አማራጭ ዋጋ ሆነ አማራጭ እቃ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ውጤት እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አቃ/ቃ/ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ ተብሎ በተዘጋጀ ከባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸውል፡፡ ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችንና የዋጋ ማቅረቢያዎችን/ ፋይናንሻል/ሰነዶች በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለባቸው ማንኛውንም ተጫራቾች የሚያስገባው ሰነድ ፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ አንድ ኦሪጅናል አንድ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የጨረታ ሰነዱን ቁጥር የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች ፣የተለያዩ ህትመት ውጤቶች፣... ዝርዝር በትክክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ ማህተም በመምታት ማስገባት ያለበት ሲሆን ሰርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያሲዙት ሲ.ፒ.ኦ. ከቴክኒክ ሰነዶችጋር በአንድ ላይ ታሽገው መቅረብ አለባቸው፡፡
- በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን ወይም አገልግሎቱን በራሳቸው ትራንስፖርት አቃ/ቃ/ክ/ከተማ ውስጥ በሚገኘው አቃ/ቃ/ክ/ፖሊስ መምሪያ በፍላጎት መግለጫው በተጠቀሰው መሰረት ጥራታቸው ተረጋግጦ የሚረከቡበ ቦታ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው፡፡ በጨረታ ሰነድ በክፍል 6 ውስጥ በሚገኘው የፍላጎት መግለጫ ላይ ... ዝርዝር ማቅረብ አለበት ፡፡
- ተጫራቾች ቃሊቲ ከሰላም ህንፃ ጀርባ በሚገኘው በአቃ/ቃ/ክ/ፖሊስ መምሪያ 4ኛ ፎቅ ....... ቁጥር ግዢና/ ፋይናንስ ቢሮ ቀርበው በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/በመክፈል መግዛት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም በማግስቱ በ11ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡00 ሠዓት ድረስ ጨረታው ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ አቃ/ቃ/ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ሲሆን በመ/ቤቱ ስብሰባ አዳራሽ ዉስጥ ይከፈታል፤
- የጨረታው መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው 3፡00 ታሽጎ ሰዓት 4፡00 ሲሆን ይከፈታል፡፡
- ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተወዳዳሪዎች የሚወዳደሩባቸዉን ዕቃዎች ሣንፕል ከጨረታዉ መከፈት ቀን በፊት መቅረብ አለባቸው፡፡ ሳንፕል ያላቀረበ ከጨረታዉ ዉድቅ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ በ/ቁጥር 011 4 39 31 96 / 011 4 71 74 84
የዕቃው ልዩ ሁኔታዎች ተያይዘዋል እነዚህም ማንኛውንም የውል ውጤት ለመመስረት አይነተኛ ክፍል ናቸው፡፡
የአቃ/ቃ/ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ
✨ messages.ai_summary
Akaki Kaliti Sub-City Police is procuring stationery, printed materials, vehicle tires, cleaning supplies, furniture, electrical/engineering and electronic goods with maintenance, medical supplies and lab equipment, uniforms, prisoner restraints, plus rented services (toilet vacuum truck, crane, hotel accommodation, vehicle rental, translation, vehicle painting) across 18 lots. Bidders need a valid business license, tax and VAT registration, supplier registration certificate, and clearance. Samples required.
