Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
  • Address አዲስ አበባ ሬስቶራንት ወረድ ብሎ የአራዳ ከ/ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት በወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ የመ/ደ/ት/ቤት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 1 26 62 73
  • Website
  • Deadline09 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ
  • opening dateበዕለቱ 4፡15
  • Categories Building Construction

የትምህርት ቤት ጥገና ስራ (ለጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት, ተቋ 001/2019) - አራዳ ወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት


የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ተቋ 001/2019 ዓ.ም

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሊያሰራው ለፈለገው ጥገና ስራ ላይ የሚሰሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ለግንባታ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የሰው ሃይል በማቅረብ የሚሰሩ በጥቃቅን አነስተኛ ዘርፍ በጥቃቅን አነስተኛ መብቃት ማህበራትን በግል ጨረታ በማወዳደር ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

ተቋራጮች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

ሎትየስራው አይነትየጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናደረጃየጨረታ ሰነድ መሸጥ የሚጀመርበት ቀንየጨረታ ማስገቢያ ቀንየጨረታ መክፈቻ ቀን
ሎት 1የወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አ/መ/ደ/ት/ቤት ጥገና ስራከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤበጥቃቅን አነስተኛ መብቃትበጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት 2፡30-10፡00 ሰዓትበጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ድረስ ብቻበጋዜጣው ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን 4፡15 ሰዓት ጀምሮ
  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ህጋዊ ዶክሜንታችሁን ዋናውንና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
  2. በዘርፉ የ2018/19 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና ከስራ ክህሎት ቢሮ የታደሰ የዕድገት ደረጃ የምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ ምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
  4. ማንኛውም ስራ ተቋራጭ ከአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ እና ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ተመዝግቦ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሳይዝ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30 እስከ 10፡00 ድረስ ከተራ ቁ.1-4 ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናውን(orginal) እና የማይመለስ ቅጂ(copy) ይዞ በመቅረብ በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አ/መ/ደ/ት/ቤት በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 ቀርበው ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  6. ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው የሥራ ቀን በዕለቱ ባለቤቱና ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በጽ/ቤት ጠዋት 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 4፡15 የሚከፈት ይሆናል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የቀረበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ያለበት በቴክኒካል ኦርጂናል ሰነድ ውስጥ ወይም ከፖስታው ውጪ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. አሰሪው መ/ቤት አሸናፊው ካሸነፈበት አጠቃላይ የስራ መጠን 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን ከማስገባታቸው በፊት የተጫራቾችን መመሪያ(Instruction to Bidder)(ITB) እንዲያነቡና የግንባታ ሳይቱን እንዲመለከቱ ይመከራል፡፡
  10. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ፣ ፋይናንሺያል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የታሸገውን ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የስራ ፕሮጀክት አይነት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም የጨረታው ፋይናንሺያል ሰነድ ላይ ያልተፈረመ ሆኖ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የተስተካከለ ዋጋ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ ከጨረታው ያሰረዛል፡፡ በተጨማሪም በስራ ዝርዝር በሙሉም ሆነ በአንድ የስራ አይነትም ላይ ዋጋ አለመሙላት ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል፡፡
  11. ተጫራቾች የሥራዎችን የዋጋ ዝርዝር እና የጨረታ መወዳደሪያ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና አድራሻቸውን አስፍሮ ማህተም በማድረግ ኢንቨሎፑን በማሸግ ማስታወቂያው በወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 4፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  12. አሸናፊ ተጫራች በስራ ዝርዝር ላይ ከገበያ ዋጋ በጣም ከፍ ያለ እና ዝቅ ያለ ዋጋ ከሞላ (Cost Break Down) ያቀርባል፡፡
  13. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የድርጅቱ የስራ ልምድና ማንኛውም በቴክኒካል የተጠየቁት ዶክመንቶችን አሰሪ መ/ቤት ኦርጂናል ዶክመንት ከሰጠው አካል የማጣራት መብት የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ጀምሮ በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  15. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ደጃች ውቤ በሚገኘው የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥ 03 በመቅረብ ወይም 0111266273 /011156 57 06 ደውለው መረዳት ይችላሉ፡፡

አራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

✨ messages.ai_summary
Repair works at Bligchita Primary and Middle School in Woreda 05, Arada Sub-City, Addis Ababa. Open to micro and small enterprises with renewed business license, tax/VAT registration, tax clearance, and registration with the Government Procurement and Property Disposal Agency.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender