ሕብረት ባንክ አ.ማ በአዲስ አበባ እና በክልል ለሚገኙ የባንኩ ቅርንጫፎች እና ለዋናው መስሪያ ቤት የእሳት አደጋ መሳሪያ ሙሌት አገልግሎት በሁለት (2) ዓመት ኮንትራት ማሰራት ይፈልጋል።
Hibret Bank S.C (ሕብረት ባንክ አ.ማ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ሕባ/019/19
ሕብረት ባንክ አ.ማ በአዲስ አበባ እና በክልል ለሚገኙ የባንኩ ቅርንጫፎች እና ለዋናው መስሪያ ቤት የእሳት አደጋ መሳሪያ ሙሌት አገልግሎት በሁለት (2) ዓመት ኮንትራት ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት የጨረታ ሰነዱን ገዝተው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከጥቅምት 05 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ የማይመለስ ብር 230.00 (ሁለት መቶ ሰላሳ) በአካውንት ቁጥር 1N0403007 አቅራቢያቸው በሚገኝ በማንኛውም የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱን ራስ አበበ አረጋይ መንገድ ሰንጋ ተራ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት ሕንፃ 19ኛ ፎቅ ግዥ ዋና ክፍል በመገኘት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ መመሪያው መሰረት የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀውን መመሪያ ያልተከተለ ተጫራች ከውድድር ሊታገድ ይችላል።
- እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ መቅረብ ያለበት ሲሆን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ተለይቶ መቅረብ አለበት።
- እያንዳንዱ ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀውን የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ወይም በታሸገ ኢንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች እስከ ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 19ኛ ፎቅ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው ከጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 19ኛ ፎቅ ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከሕብረት ባንክ ውጭ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114 67 32 08 ወይም 011 470 6541 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ሕብረት ባንክ አ.ማ
✨ messages.ai_summary
Hibret Bank seeks a two-year contract for fire extinguisher refilling services for its branches in Addis Ababa and the regions, plus its head office. Eligible bidders must hold a valid business license and submit sealed technical and financial envelopes per the tender document.
