የጽህፈት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ ጽዳት፣ ጀኔሬተር፣ ደንብ ልብስ፣ ግንባታ እቃዎችና ተሽከርካሪ መለዋወጫ ግዥ (13 ሎቶች) - ምዕራብ ኦሞ ዞን መኢኒት ሻሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
- ሎት 1- የጽህፈት መሳሪያዎች
- ሎት 2- ኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ እቃዎች
- ሎት 3- ፈርኒቸሮች
- ሎት 4- የጽዳት እቃዎች
- ሎት 5- ጀኔሬተሮች
- ሎት 6- የስፖርት ትጥቅ እና ቁሳቁሶች
- ሎት 7- የደንብ ልብስ
- ሎት 8- የህንጻ መሳሪያዎች /የግንባታ እቃዎች/ Industrial materials/
- ሎት 9- አትክልት እና ፍራፍሬ ዘር
- ሎት 10- የህትመት ውጤቶች
- ሎት 11- የእንስሳት መድኃኒት እና የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶች
- ሎት 12- የባለ አራት እግር ተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃ
- ሎት 13- የባለ አራት እግር ተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት /ሰርቪስ/ እጅ ጉልበት ዋጋ
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርት
- በዘርፉ የታደሰ ስራ ንግድ ፍቃድ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤
- የዘመኑ ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ፤
- የመንግስት ግዥ አቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ከባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ በኢትዮጵያ ብር 5000/አምስት ሺህ ብር/ ከቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ዶክመንት ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ የመንግስት ስራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ዝርዝር መረጃ የያዘውን ሰነድ ሲውሰዱ /ለመግዛት/ በወረዳው ገቢዎች ቢሮ የማይመለስ ብር 300/ ሶስት መቶ ብር/ ገቢ በማድረግ በመ/ቤታችን የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዋና ስራ ሂደት በሚገኙበት ቢሮ ቁጥር 08 ሰነዱን መውሰድ ይኖርባችኋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የፋይናንሺያል እና የቴክኒካል መወዳደሪያ ዶክመንቶቻችሁን በተለያየ ፖስታ ኦርጅናሉን ከአንድ ኮፒ ፋይናንሺያል ከአንድ ኮፒ ለየብቻ በማሸግ የድርጅታችሁን ማህተም የሚገልጽ ፊርማ እና ማህተም ያለው ዶክመንት እስከ 16ኛው ቀን /ጨረታውን የመከፈቻ እለት/ በመኤኒት ሻሻ ወረዳ ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የግዥ እና ንብረት አስተዳደር በሚገኙበት ቢሮ ቁጥር 08 ለዚሁ አላማ በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ ቢገኙም/ ባይገኙም በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈት ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት እንደ አስፈላጊነቱ ተጫራች ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ በዚህ ስልክ ቁጥር መደወል ይችላሉ፡፡ 0914237063 0934234926
ማሳሰቢያ፡- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/በምዕራብ ኦሞ ዞን የመ/ሻሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Procurement of stationery, electronics, furniture, cleaning supplies, generators, sports equipment, uniforms, construction materials, seeds, printed materials, veterinary and medical supplies, and vehicle spare parts and repair services, in 13 lots. Bidders must have a renewed business license, VAT registration, TIN, tax payment proof, and government supplier registration.
