Tender Detail

Tender Details

  • Company የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን
  • Address ወልቂጤ ከተማ ወደ ወልቂጤ ኢንዲስትሪያል ኮሌጅ በሚወስደው አስፋልት መንገድ ላይ የድሮው የወልቂጤ ከተማ ስፖርተኞች ማደርያ ጊቢ ውስጥ : በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት : ኢትዮጵያ, Phone: 011 365 9932
  • Website
  • Deadline30 Oct 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 300.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 300,000.00 (የባንክ ዋስትና ወይም CPO)
  • opening dateበዚያው ቀን ከቀኑ 8፡30
  • Categories Machinery Spare Parts , Vehicle Spare Parts

ለተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች የባትሪ ግዥ (ማ/ኢ/መ/ባ/ባት/03/18) - የማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን


የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ማ/ኢ/መ/ባ/ባት/03/18

መ/ቤታችን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ለተለያዩ አሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች አገልግሎት የሚውል ባትሪዎች ግዥ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፡-

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም አገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፣ የመንግስት መሥሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የፋይናንሻል ፕሮፖዛል አንድ ዋና እና ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ፕሮፖዛሉን አንድ ዋና እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያውን በተለየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ) ብቻ በመክፈል በባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፡፡
  5. አቅራቢዎች ጨረታውን ገቢ የሚያደርጉት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያው ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ካላቸው የፋይናንስ ተቋም በቅድመ- ሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ (CPO) ለአንድ ማሽን ብር 300,000.00(ሦስት መቶ ሺህ) ብቻ በማሰራት ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡በኢንሹራንስ ዋስትና የሚቀርብ የጨረታ ማስከበርያ ተቀባይነት የለውም፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጪ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  8. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ለበለጠ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡

ስልክ ቁጥር 0113659932
ወልቂጤ ኢትዮጵያ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም

✨ messages.ai_summary
Central Ethiopia Roads Authority seeks eligible suppliers for vehicle and machinery batteries. Bidders must submit a valid business license, supplier certificate, government tender participation certificate, and VAT registration. Open to any supplier regardless of nationality.
Save Tender