Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
  • Address ሳሪስ አቦ ፋፋ የምግብ አክሲዮን ጎን 200 ሜትር ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114709095
  • Websitehttps://ethioagri.com/
  • Deadline29 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceለእያንዳንዱ ሎት ብር 1,000 (የማይመለስ)
  • Bid Securityሎት 1፡ ብር 200,000፤ ሎት 2፡ ብር 1,000,000፤ ሎት 3፡ ብር 200,000 (CPO ወይም unconditional ባንክ ጋራንቲ)
  • opening dateበየዕለቱ 4፡30
  • Categories Building Construction

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከታች ቀጥሎ ከሎት አንድ እስከ ሎት ሶስት ድረስ የተዘረዘሩትን የመጋዘን እና የአጥር ግንባታ ሥራዎችን ለማከናወን ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)


የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢግ.ሥ.ኮ./ብግጨ/03/2019

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከታች ቀጥሎ ከሎት አንድ እስከ ሎት ሶስት ድረስ የተዘረዘሩትን የመጋዘን እና የአጥር ግንባታ ሥራዎችን ለማከናወን ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የሎት ቁጥር የጨረታ አይነት እና ቦታው ደረጃ የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ (የማይመለስ) የመዝጊያ ቀን የመዝጊያ ሰዓት የመክፈቻ ሰዓት
1 ሎት 1 የአሶሳ ቅርንጫፍ የአጥር ግንባታ (አሶሳ) GC5/BC4 እና ከዚያ በላይ 1000 ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም 4፡00 4፡30
2 ሎት ሁለት የኮፈሌ ቅርንጫፍ መጋዘን እና አጥር ግንባታ(ኮፈሌ) GC5/BC4 እና ከዚያ በላይ 1000 ጥቅምት 20 ቀን 2019 ዓ.ም 4፡00 4፡30
3 ሎት ሦስት የአሰላ ቅርንጫፍ የኢተያ መጋዘን አጥር ግንባታ (ኢተያ) GC5/ BC4 እና ከዚያ በላይ 1000 ጥቅምት 23 ቀን 2019 ዓ.ም 4፡00 4፡30

በመሆኑም ከላይ በዝርዝር እንደተገለፀው የመጋዘን እና የአጥር ግንባታ ሥራ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ቴክኒካል መስፈርት መሰረት ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል ፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ፤

  1. ደረጃቸው ከላይ በሠንጠረዥ ውስጥ እንደተገለፀው ሆኖ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፤ቲን ቫት፤ የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ እና ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ፤ በEGP የአቅራቢዎች ሊስት የተመዘገበ እንዲሁም ከገቢዎች ሚ/ር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ ጉምሩክ ከባቡር መነሻ ፊት ለፊት በሚገኘው አዋሽ ባንክ በኩል ወደ ውስጥ በሚያስገባው መንገድ ገባ ብሎ በሚገኘው የቀድሞ የግብርና ግብዓት አቅርቦት ዘርፍ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 306 ግዥ ክፍል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከላይ በየሎቱ በተገለፀው ብር መሰረት በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ አንድ ተጫራች ሦስቱንም ሎቶች (3) መግዛት ይችላል ነገር ግን መጫረት የሚችለው በአንድ ሎት ብቻ ነው፡፡
  2. ተጫራቾች ለጨረታው በተዘጋጀው ሰነድ ላይ የሚሞሉት የነጠላ ዋጋ ብቻ በግልፅ የሚታይና ስርዝ ድልዝ የሌለበት መሆን ይኖርበታል፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ለሎት ሁለት ብር 1,000,000.00(አንድ ሚሊዮን ብር) ሲሆን ለሎት አንድ እና ለሎት ሦስት ለእያንዳንዳቸው ሎቶች ብር 200 ሺህ በሲ.ፒ.ኦ.ወይም በባንክ ጋራንቲ (unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታ ዋስትናው ለብቻው በአንድ ፖስታ ውስጥ ተደርጎ ከኦርጂናል ቴክኒካል ሰነድጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ የጨረታው ዋጋ ለ120 ቀናት የጸና ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ዶክመንት መሰረት ቴክኒካል ኦርጂናልና ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሽያል በተለያዩ ፖስታ በማድረግ ፋይናንሽያል ሰነዱ ዋና እና ኮፒ በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. እያንዳንዱ ጨረታ የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቀን እና ሰዓት ከላይ በሠንጠረዥ ውስጥ በተገለፀው መሰረት ሁኖ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የቴክኒካል ጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ስነሥርዓት ይከናወናል፡፡
  6. ከኮርፖሬሽኑ ጋር ውለታ ገብተው ግንባታ ጨርሰው ያላስረከቡ ወይንም የግንባታ አፈፃፀማቸው ከ70% በታች የሆኑ ተቋራጮች በጨረታው ላይ መወዳደር አይችሉም ፡፡
  7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
ስልክ+251911984467/+251910567578
አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

✨ messages.ai_summary
The Ethiopian Agricultural Businesses Corporation seeks contractors for warehouse and fence construction works across three lots (Assosa, Kofele, and Iteya). Bidders must hold GC5/BC4 or above grades, valid trade license, TIN, VAT, tax clearance, renewed Ministry of Construction competency certificate, and EGP supplier registration. One bidder may buy all three lots but bid on only one.
Save Tender