Tender Detail

Tender Details

  • Company City Administration of Addis Ababa Construction Design, Building and Consultation Enterprise (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት)
  • Address አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 4 62 14 57
  • Websitehttps://addisconstructionwork.gov.et/
  • Deadline28 Oct 2026, 10:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300(ሶስት መቶ ብር)
  • Bid Securityለሎት 1 ብር 60,000.00 (ስልሳ ሺህ ብር) ለሎት 2 ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ለሎት 3 ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀናት የባንክ ዋስትና (un conditional bid bond guarantee)
  • opening dateበዚሁ ዕለት ከረፋዱ 5:00 ሰአት ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል
  • Categories Generators , Cargo Vehicle , Construction Machinery And Vehicles

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ከዚህ በታች በሎት ተከፋፍሎ በተቀመጠው መሰረት በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል::

City Administration of Addis Ababa Construction Design, Building and Consultation Enterprise (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት)


ጀነሬተሮች እና የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ግዥ ግልጽ ጨረታ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር የኮ/ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ 06/2018

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ከዚህ በታች በሎት ተከፋፍሎ በተቀመጠው መሰረት በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል::

ሎት 1:- ጀነሬተሮች

ሎት 2:- የኤሌክትሪክ አውቶሞቢሎች

ሎት 3:- ከባድ መኪኖች

ስለሆነም :-

  1. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በዘርፉ የተሰጠ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፤ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ኮፒ አያይዘዉ ማቅረብ የሚችሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ግንባታና ማማከር ድርጅት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ::
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 60,000.00 (ስልሳ ሺህ ብር) ለሎት 2 ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ለሎት 3 ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀናት የባንክ ዋስትና (un conditional bid bond guarantee) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 5:00 ሰአት ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::
  4. የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ግንባታና ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ:-በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ ስልክ ቁጥር 0913-56-49-36/ 0911-15 60 26

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት

✨ messages.ai_summary
Addis Ababa Construction Design, Building and Consultation Enterprise seeks bidders for generators, electric automobiles, and heavy vehicles, divided into three lots. Eligible bidders must hold a renewed trade license, business registration certificate, tax payment proof, VAT registration, and be on the suppliers list.
Save Tender