Tender Detail

Tender Details

  • Company ጉምሩክ ኮሚሽን አዋሽ ቅ/ፅቤት
  • Address , Phone: ..........
  • Website
  • Deadline21 Oct 2026, 9:45 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100(አንድ መቶ ብር)
  • Bid Securityለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
  • opening dateለግልጽ ጨረታ 11/02/2019 በ14/02/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ 11/02/2019 እና በ14/02/2019 5:00 ሰዓት ይሆናል፡፡
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Electronics Materials , Cloth And Shoes

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 11/02/2019 እና በ14/02/2019 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽን አዋሽ ቅ/ፅቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 11/02/2019 እና በ14/02/2019 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክለት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣ የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እንዲመጣሎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የጨረታ መስፈርቶች-

  1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከል ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን 11/02/2019 እና በ14/02/2019 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 3:45 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ፡፡
  3. ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (እስኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ፤
    ተ.ቁየጨረታ ቦታየጨረታው ዓይነትለጨረታ የቀረቡ እቃዎችየዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከየጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት
    1ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ ቤትግልጽ ጨረታ እና በሐራጅጫማዎች አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ የሞባይል ቀፎና አሰሰሪ - ኤሌክትሮኒክስ፣ ምግብ ነክ የስፖርት እቃዎች፣ የእጅ ሰዓት ኮስሞቲክስ፣ መነፅር፣ ጊጣ ጌጦች የሳሙና ፋብሪካ አካል ማሽነሪ ተሽከርካሪ የቡና ረከቦት እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎችለግልጽና ለሐራጅ ጨረታ 11/02/2019 እና በ14/02/2019 እስከ ጠዋቱ 3:45ለግልጽ ጨረታ 11/02/2019 በ14/02/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ 11/02/2019 እና በ14/02/2019 5:00 ሰዓት ይሆናል፡፡
  5. የጨረታው መከፈቻ ቦታ:- በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
  6. የጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (c.p.o) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  7. ከአሸፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል፡፡
  8. ከላይ በተ.ቁ.7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
  9. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ለጨረታ የቀረበ የተሽከርካሪ መረጃ

ተ.ቁየተሽከርካሪ አይነትየሻንሲ ቁጥርየሞተር ቁጥርሞዴልየስሪት ሀገርየምርት ዘመንየፈረስ ጉልበት(cc)
1HYUNDAI TUCSONKMH-J381AD-GU08 5670D4HAEH61 6328F/ R3/50384KOREA20151997

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 022-224-1402 ደውለው ስለ ጨረታው መረጃ መጠየቅ ይቻላል፡፡

በጉምሩክ ኮሚሽን የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Awash Customs Office seeks to sell various confiscated contraband goods via open and auction tender at Kaliti Customs Office. Items include clothing, vehicle spare parts, mobile phones, electronics, food, sports goods, watches, cosmetics, eyeglasses, jewelry, soap factory machinery, vehicles, coffee beans, and more. Bidders need a renewed trade license, VAT registration, tax clearance, and recent VAT activity certificate.
Save Tender