በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን የብረታ ብረት ሽያጭ ጨረታ፡፡
FDRE Industrial Parks Development Corporation Kilinto Special Economic Zone
የጨረታ ማስታወቂያ
ሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ
የቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን የብረታ ብረት ሽያጭ ጨረታ
የመሥሪያ ቤቱ ስም:- በኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን
የሽያጭ ስም:- የብረታብረት ሽያጭ
የሽያጭ መለያ ቁጥር:- ቂ/ል/ኢ/ዞ/ንማግጨ/01/2019
- በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን የብረታ ብረት ሽያጭ ጨረታ
- አስፈላጊ የሕጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶች፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የተ.እ.ታ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት
- ጨረታው ሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ሲሆን የቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን በሚዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሰረት ሕጋዊ ሆነው ለሚቀርቡ ተጫራቾች በሙሉ ክፍት ነው፡፡
- የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚፈልግ ተጫራች በልዩ ኢኮኖሚክ ዞኑ በመቅረብ ከሰኞ እስከ ሐሙስ ጠዋት ከ2:30 እስከ 6:30 ከሰዓት ከ7:30-11:30 እንዲሁም አርብ ጠዋት ከ2:30 -5:30 ከሰዓት ከ7:30-11:30 ቅዳሜ ጠዋት ከ2:30-6:00 ድረስ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት እና ንብረቱን ማየት ይችላል፡፡
- የመወዳደሪያ ሰነድ የሚያስገቡ ተጫራቾች እስከ ጥቅምት 9 ቀን 2019ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ በልዩ ኢኮኖሚክ ዞኑ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በዚሁ ቀን 8:00 ሰዓት ተዘግቶ 8:30 ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑ ከዚህ ሰዓት በኋላ የሚመጣ የመወዳደሪያ ሰነድ ውድቅ የሚደረግ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 25,000.00( ሃያ አምስት ሺህ ብር) ቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን በሚል በሲፒኦ ወይም አንኮንዲሽናል ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ድርጅቱ በማንኛውም ጊዜ የአሸናፊነት ውጤት ከመግለፁ በፊት ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሕንፃ
አድራሻ:- ክፍለ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 09/10(ከኮዮ ፈጬ አደባባይ ሳይደርሱ 500 ሜትር ርቀት ላይ)
የኮርፖሬት ሀብት ማኔጅመንት 1ኛ ፍሎር
ስልክ:- +251951414178
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን
✨ messages.ai_summary
Sale of ferrous and non-ferrous scrap metal by the Industrial Parks Development Corporation's Kilinto Special Economic Zone. Open to legally registered bidders who must submit a valid business license, commercial registration certificate, VAT certificate, and taxpayer identification certificate. Bidders may inspect the metal and must meet the stated requirements.
