በድሬዳዋ አስተዳደር የድልጮራ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ ለ 2 (ሁለት ዓመት) የሚውል የጥበቃ አገልግሎት በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ህጋዊና ብቁ ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር የድል ጮራ ሆስፒታል
በድጋሚ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ድ/ጬ/ድ/ጨ/ሆ/03/19
በድሬዳዋ አስተዳደር የድልጮራ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ ለ 2 (ሁለት ዓመት) የሚውል የጥበቃ አገልግሎት በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ህጋዊና ብቁ ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት በጨረታው ላይ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች
- ተጫራቾች በዘርፉሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ለ2019 ዓ.ም ግብር የከፈሉ፤ በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በመንግስት ግዢ አቅራቢ የተመዘገቡና የተመዘገቡበትን ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ከፌዴራል ፖሊስ የታደሠ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የታክስ መለያ ቁጥር (TIN No) ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺ ብር) በመክፈል በድል ጮራ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር A/02 በመቅረብ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም (CPO) ከጨረታው ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ መቀበያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ የሚከፈትበት ቀን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሠዓት ተዘግቶ ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ ግዢ ፋ/ን/አስ ዳይሮክቶሬት ቢሮ ቁጥር A/02 ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ እንደተገለፀለት አስፈላጊውን የጨረታ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከሆስፒታሉ ጋር ውል መፈረም አለበት፡፡ ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሠረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን እና ፊርማቸውን እንዲሁም የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ከግል ስራና አገናኝ ኤጀንሲ በአገር ውስጥ ስራና ሠራተኛ የማገናኘት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- በድሬዳዋ አስተዳደር የድል ጮራ ሆስፒታል
ስልክ ቁጥር፡- 025-211-5692/0982540408/0901103211፤ ፖስታ ሳጥን ቁጥር 177
በድሬዳዋ አስተዳደር የድልጮራ ሆስፒታል
✨ messages.ai_summary
Dire Dawa Administration Dilchora Hospital seeks eligible bidders for a two-year security service contract. Bidders must hold a valid trade license, VAT registration, tax clearance, TIN, supplier registration, and a federal police-cleared license.
