Tender Detail

Tender Details

  • Company Awash Bank S.C (አዋሽ ባንክ አ.ማ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115571107
  • Websitehttps://awashbank.com/am-et/
  • Deadline27 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price100(አንድ መቶ ብር)
  • Bid Securityየ1 (አንድ) ወር ኪራይ መነሻ ዋጋ ¼ኛ (CPO)
  • opening dateጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

አዋሽ ባንክ አ.ማ. በአሰላ ከተማ የሚገኘውን ደረጃውን የጠበቀ ባለ 5(አምስት) ወለል ሕንፃ ለንግድ፣ ለቢሮ፣ ለካፌና ሬስቶራንት እንዲሁም ለተለያዩ አገልግሎቶች በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

Awash Bank S.C (አዋሽ ባንክ አ.ማ)


የሕንፃ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

አዋሽ ባንክ አ.ማ. በአሰላ ከተማ የሚገኘውን ደረጃውን የጠበቀ ባለ 5(አምስት) ወለል ሕንፃ ለንግድ፣ ለቢሮ፣ ለካፌና ሬስቶራንት እንዲሁም ለተለያዩ አገልግሎቶች በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከታች የተዘረዘሩትን የጨረታውን መመሪያዎች በማሟላት በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በየትኛውም የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ በሒሳብ ቁጥር 01540000544500 በተጫራቹ ስም ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኙን አሰላ ከተማ በሚገኘው አዋሽ ባንክ አሰላ ቅርንጫፍ በማቅረብ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት ለጨረታው መወዳደሪያ የሚሆን የ1 (አንድ) ወር ኪራይ መነሻ ዋጋ ¼ኛ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ሴኪዩሪቲ ቦንድ) ተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) በአዋሽ ባንክ አክስዮን ማህበር ስም በማሰራት በታሸገ ኤንቬሎፕ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ አሰላ ከተማ በሚገኘው የአዋሽ ባንክ አሰላ ቅርንጫፍ ለጨረታው በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ከጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ሴኪዩሪቲ ቦንድ) ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት አሰላ ከተማ በሚገኘው የአዋሽ ባንክ አሰላ ቅርንጫፍ ውስጥ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  5. የጨረታው አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የ3 ወራት የኪራይ ክፍያ በቅድሚያ በመክፈል ውል መፈፀም ይጠበቅባቸዋል፣ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ክፍያውን ፈጽመው የኪራይ ውል ካልፈፀሙ የጨረታው ውጤት ተሰርዞ ያስያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡
  6. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-530-31-02/04፣ ወይም 022-331-28-75 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

አዋሽ ባንክ አክስዮን ማህበር

✨ messages.ai_summary
Awash Bank invites bids to rent a five-storey building in Asela for commercial, office, café, restaurant, and other service uses. Bidders must meet the tender requirements and submit a CPO bid security.
Save Tender