Tender Detail

Tender Details


ቋሚና አላቂ ዕቃዎች እና የአገልግሎት ግዥ (15 ሎቶች፣ አ/አ/ከ/ፍ/ቤት/01/2019) - የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች (ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት)


የጨረታ ማስታወቂያ

መለያ ቁጥር አ/አ/ከ/ፍ/ቤት/01/2019

የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቋሚና አላቂ ዕቃዎች እና የአገልግሎት ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤

  • ሎት.1. አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች
  • ሎት.2. የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች
  • ሎት.3 አላቂ የጽዳት እቃዎች
  • ሎት.4. የደንብ ልብስ
  • ሎት.5. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  • ሎት.6 የተለያዩ ፈርኒቸሮች
  • ሎት.7. የኤሌክትሪክ ዕቃዎች
  • ሎት-8 የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች
  • ሎት.9. የተለያዩ የህትመት ሥራዎች
  • ሎት.10. የደንብ ልብስ ስፌት
  • ሎት.11. የኤሌክትሮኒክስ እና ማሽነሪ ጥገና ስራዎች
  • ሎት.12. የቢሮ እና የቤት እቃዎች ጥገና ስራ
  • ሎት.13. የቢሮ ጥገና እና የእድሳት ስራዎች
  • ሎት.14. የተለያዩ የውሃ መስመር ስራዎች
  • ሎት.15. የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ እና የጥገና ስራዎች
  1. የግዥ መለያ ቁጥር አ/አ/ከ/ፍርድ ቤቶች 01/2019
  2. ግዥው ግልጽ ጨረታ ነው
  3. ጨረታ ሰነድ የወጣበት መስከረም ወር 2019 ዓ/ም

    ተጫራቾች ህጋዊ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ፤ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆኑ ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት እና የጨረታ መስተናገድ ደብዳቤ የሚያቀርቡ፣ ለሚወዳደሩበት እቃ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ የሚችሉ እንዲሁም ቋሚ የስራ ቦታ ወይም ቢሮ ያላቸው ሆነው በቅድመ ምዝገባ ወቅት የቀረቡ ድርጅቶችን ወይም የሥራ ቦታቸውን ማሳየት ፍቃደኛ የሆኑ ከዚህ በፊት ከፍርድ ቤቱ ጨረታ አሸንፈው በበፊቱ ውል መሰረት ግዴታቸውን የተወጡ ድርጅቶች፤

  1. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ከግዥ ፈጻሚ የአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ቢሮ 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ ፡፡
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ ለተገለፁት ዕቃዎች ለተወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ (C.P.O) ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ከሎት 1 እስከ ሎት 15 ድረስ ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት ከጠቅላላ ዋጋ 2 % ፐርሰንት ወይም ተጫራቾች በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ያደራጃቸው መስሪያ ቤት ለፍትህ ብሮ የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት እንዲያወቀው ያደረገ ደብዳቤ የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ በታሸገ ኤንቨሎፕ በፊርማና ማህተም አድርገው እና የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በሚመለከተው የፍ/ቤቱ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታውን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  4. ተጫራቾች ናሙና የሚያስፈልጋቸውን እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ ከ1 ቀን በፊት ለሚጫረቱበት ሎት እና ለሚጫረቱበት እቃዎች ናሙና በሚመለከተው ቢሮ ቀርበው በማስመዝገብ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።

    ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች የአንዱን ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ VAT ጭምር ማካተት ይኖርባቸዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ጨረታውን ለመገምገም ያሉትን መስፈርቶች ዕቃዎቹ ፍርድ ቤቱ ባስቀመጠው ስፔስፊኬሽን መሰረት ወይም የሚቀርበው ናሙና ጥራት፤ አገልግሎት ዋጋ እና አቅራቢው የሚያቀርብበት ጊዜ ግምት ውስጥ ይገባል።

  5. ፍርድ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
  6. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  7. በሎቱ የሚገለፁ ተወዳዳሪ ድርጅቶች በዘርፉ የሚሰሩ ድርጅቶች ብቻ መሆን አለባቸው።
  8. ኮፒ እና ኦሪጅናል ኢንቨሎፕ በተናጠል (በየሎቱ) በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. የሚወዳደሩበትን ሎት ለየብቻ ነጣጥለው በፖስታው ላይ ሎቱን በመፃፍ ማስገባት አለባቸው። ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የማያሟሉ አቅራቢዎች ከጨረታው ውጪ የሚደረጉ ይሆናል

አድራሻ፡- ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሜክሲኮ ፌዴራል ሸዋ አጠገብ የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ላይ አዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 102 ሲሆን

ስልክ ቁጥር፡- 011-515-70-40

አዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት

✨ messages.ai_summary
Addis Ababa City Courts seek suppliers for durable and consumable goods and services across 15 lots, including stationery, furniture, cleaning supplies, uniforms, electronics, printing, vehicle parts, and maintenance works. Bidders must hold a valid trade license, tax clearance, VAT and TIN certificates, and a permanent office.
Save Tender