የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ እና መጋዘን ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ እቃዎች በጅምላ እንዲሸጡ በተወሰነው መሰረት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ፣ ያገለገለ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት (FDRE Refugees and Returnees Service)
ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ እና መጋዘን ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ እቃዎች በጅምላ እንዲሸጡ በተወሰነው መሰረት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ፣ ያገለገለ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ባወጣው የዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የሽያጭ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት መ/ቤት ቅጥር ግቢ የፋይናንስ ቢሮ በመገኘት እና ከፍያ በመፈጸም ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ከመስከረም 29/2019 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት/Refugees and Returnees Service /በሚል የተዘጋጀ የክፍያ ማዘዣ / CPO/ የባንክ ዋስትና /Bank Gurantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራቾ ከመስከረም 29,2019 እስከ ጥቅምት 10,2019 ዓ.ም ድረስ ባሉት የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ጉለሌ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ በመገኘት ዕቃዎቹን መመልከት ይችላል፡፡ ቅዳሜና እሁድ የስራ ቀናት አይደሉም፡፡
- ጨረታው ጉለሌ እንቁላል ፋብሪካ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ የሚከናወን ሲሆን የጨረታው ሳጥን ጥቅምት 10 ቀን 2019 ከቀኑ 4፡30 ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲፒኦ ከሚከፍሉበት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋስትና በ3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎቹን መረከብ አለባቸው፡፡
- በተራ ቁጥር 6 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራች ለጨረታው ማስከበርያ ያስያዘው ሲፒኦ ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ገቢ በማድረግ የተሻለውን አማራጭ የመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251910474668 ወይም 251911569913 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት
✨ messages.ai_summary
The Refugees and Returnees Service invites bidders to an open tender for the bulk sale of various items held at its headquarters near the Egg Factory, including assorted electronics, used vehicle spare parts, and scrap metals. Bidders must pay a non-refundable fee for the sale document and submit a bid security.
