Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline09 Nov 2026, 4:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O
  • opening dateየተጫራቾች ምዝገባ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

በኦሮሚያ ክልል በሱሉልታ ከተማ ሸፋኔ ሳይት በአቶ መስፍን ቸሩ ስም የተመዘገበ የቦታ ስፋት 200 ካ/ሜ የሆነ ቤት ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ወ/ሮ ትዝታ ጌታነህ እና በፍ/ባለዕዳ አቶ መስፍን ቸሩ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.115687 በ06/05/2012ዓ.ም እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.162383 በ7/7/2012ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በኦሮሚያ ክልል በሱሉልታ ከተማ ሸፋኔ ሳይት ብሎክ ብሎክ 44 ቁጥር 13 የካርታ ቁጥር SUL/01/3553/99 የሆነ በአቶ መስፍን ቸሩ ስም የተመዘገበ የቦታ ስፋት 200 ካ/ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ መነሻ 1,884,042.06/10 ( አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰማንያ አራት ሺህ አርባ ሁለት ከ06/100) ሆኖ የትራንዝክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጅ ሽያጩ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ C.P.O የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡

በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤ/ስም C.P.O አሠርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሠርት ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን ፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር :- +251112730852

በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
A 200 sq.m house in Sululta Town, Oromia, registered under Mesfin Cheru, is sold at auction by the Federal Courts Execution Office. Bidders must visit the property beforehand and deposit a quarter of the estimated value via a verified C.P.O. The winner must pay the full amount within 15 days.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender