ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ - በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 01 የቤት ቁጥር 942 ለመኖሪያ እና ለድርጅት የሆነ ይዞታ - በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ስንዱ ደገፋ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ንጋቱ አፍረስ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.333136 በ26/06/2017ዓ.ም እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.136054 በቀን በ25/11/2016ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ.145518 በቀን 03/07/2017ዓ.ም በኮ/መ/ቁ.145518 በቀን 27/04/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 01 የቤት ቁጥር 942 የካርታ ቁጥር ወ1/ውዝ01/1703/32188/00 የሆነ የቦታ ስፋት 1272.34 ካ/ሜ ሲሆን በይዞታው በሰፈሩ ስም ኢትዮጵያ በኪራይ ውል የተያዘው 145.2 ካ/ሜ በብሎኬት የታጠረ ሲሆን ይዞታው ለመኖሪያ እና ለድርጅት የሆነ የሐራጅ መነሻ 44,126,633.16 (አርባ አራት ሚሊዮን አንድ መቶ ሃያ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ሰላሳ ሶስት ከ16/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም / በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡ ፡ ስለሆነም ' በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.145518 በቀን 08/11/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በድጋሚ ሐራጅ ጨረታ ሆኖ 1/4ኛ በር 11,031,658,29 ( አስራ አንድ ሚሊዮን ሰላሳ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ ስምንት ከ29/100) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡የተጫራቾች ምዝገባ 9:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ _ ባሉት _ አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ _ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድሮስ ከጠዋቱ በ3:30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
ከ1/4ኛው አስበልጠም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ _ የሆነው ግለሰብ _ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤ/ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
