Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Bank S.C (አማራ ባንክ አ.ማ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-558-2660
  • Website
  • Deadline06 Nov 2026, 9:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ ወይም ሃያ አምስት በመቶ (25%) (C.P.O)
  • opening dateጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም.
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

አማራ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድር ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Amhara Bank S.C (አማራ ባንክ አ.ማ)


የሐራጅ ማስታወቂያ

የሐራጅ ቁጥር፡ አማራ ባንክ/51/2019

አማራ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድር ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

ተ.ቁየተበዳሪው ስምየንብረት አስያዥ ስምአበዳሪው ቅርንጫፍየንብረቱ አድራሻ ከ/ከተማከተማወረዳቀበሌየቦታው ስፋትየባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥርየንብረቱ ዓይነት/ የይዞታው አገልግሎትየጨረታ መነሻ ዋጋ /ብር/ጨረታው የሚካሄድበት ቀንሰዓትቦታ
1አንዋር መሀመድ አብዱልቃድርአንዋር መሀመድሎጊያሎጊያሎጊያ-031224 ካ.ሜትርሠ/ሎ/ ከ/ሐ/491/17ለድርጅት11,341,159.19ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም.ከ4:00 እስከ 5:00 ሰዓትአማራ ባንክ አ.ማ ደሴ ዲስትሪክት ቢሮ
2አለሙ ቢተው ትዛዙወ/ሮ ጥሩዓለም አጅት ዘሪሁንፍኖተ ሰላም-ፍኖተ ሰላም04-250 ካ.ሜ5918ለ-2014ለመኖሪያ1,307,585.52ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም.ከ 3:00 እስከ 4:00 ሰዓትአማራ ባንክ አ.ማ ባህር ዳር ዲስትሪክት ቢሮ
3ፀሀይነሽ ሆኔ ኃይሌፀሀይነሽ ሆኔ ኃይሌደብረታቦር-ደብረታቦር-01650 ካሬ ሜትር8.2/27/898/14መኖሪያ14,994,071.19ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም.ከ 4:00 እስከ 5:00 ሰዓትአማራ ባንክ አ.ማ ባህር ዳር ዲስትሪክት ቢሮ

ማሳሰቢያ

  1. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ ወይም ሃያ አምስት በመቶ (25%) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (C.P.O) ብቻ በአማራ ባንክ አ.ማ ስም በማሠራት፣ በማስያዝ እና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  2. ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በጽሑፍ ሲደርሰው ብቻ ነው፡፡
  3. የጨረታ አሸናፊው አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ አይመለስለትም፣ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡ ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በዕለቱ ይመለስላቸዋል፡፡
  4. የሐራጁ አሸናፊ /ገዥ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግሥት የሚከፈሉ ክፍያዎችን የሊዝን ክፍያን ጨምሮ፣ ግብር፣ በዋጋው ላይ ሚታሰብ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) ካለ ከስም ማዛዋወሪያ ጋር የተገናኙ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታክስ እና ግብሮች ገዥው/አሸናፊው/ ይከፍላል፡፡
  5. ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ (የቀበሌ፣ የመንጃ ፍቃድ፣ ፓስፖርት ወይም ብሄራዊ መታወቂያ) መያዝ ይገባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ግለሰብ ሥልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የጸደቀ መመስረቻ ጽሑፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ ቃለጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  6. ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግሥታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
  7. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም ከወርካውትና ሪከቨሪ ክፍል ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ ጨረታው ከመካሄዱ ከ5 ቀን በፊት መጎብኘት ይችላል፡፡
  8. ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል፡፡ ነገር ግን ተበዳሪውም ሆነ መያዣ ሰጪው ባይገኙ ጨረታው በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
  9. ንብረቱን/ቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም፡፡ ገዥው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡
  10. በባንኩ የብድር ፖሊሲ፣ መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ ፤
    - እስከ 100% ድረስ ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
    - በንብረቱ ላይ የምርት ተግባር ለሚያከናውኑ ገዥዎች ባንኩ ተጨማሪ ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
    በተጨማሪም ለባንኩ የተሻለ ጥቅም የሚያስገኝ ከሆነ ባንኩ ለመደራደር ዝግጁ ነው፡፡
  11. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መነሻ ሰዓት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡
  12. በወንድ እንቀጽ የተጠቀሰው ለሴት እና ሕጋዊ ሰውነት ላላቸው ድርጅትም ያገለግላል፡፡
  13. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ለበለጠ ማብራሪያ አማራ ባንክ አ.ማ 0115 58 27 64 ወይም 011 5 58 41 89 በሥራ ሰዓት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አማራ ባንክ

✨ messages.ai_summary
Amhara Bank is selling repossessed properties via open auction: land, houses, buildings, and warehouses across various locations. Bidders must present ID and, for entities, legal registration documents. Winners pay all transfer taxes and fees. The bank may arrange up to 100% financing for eligible winners.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender