በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የቤት ቁጥር 1501 የሆነውን ቤት በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት በሐራጅ ይሸጣል፡፡
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍርድ ባለመብት ሰርካለም ለገሰ እና በፍርድ ባለእዳ እነ ፈለቀች ደገፉ መካከል ስላለው አፈፃፀም የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 199640 በቀን 18/07/2017ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ 207997 በቀን 05/09/2017ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የቤት ቁጥር 1501 የሆነውን ቤት የይዞታ መለያ ቁጥር AA000080400698/2 የቦታ ስፋት 223.50ካ/ሜ ሲሆን የወለሉ ስፋት 95.07ካ/ሜ+7.13ካ/ሜ ሆኖ የሽያጭ ዋጋ መነሻ ግምት ብር 9,736,533 ( ዘጠኝ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰላሳ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ሰላሳ ሶስት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል። የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፤ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጣቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ./ጽ/ቤት ስም C.P.O አሠርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ./ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ _ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +25111 2730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
