የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች የሽያጭ ጨረታ – ቤንሻንጉል ጉሙዝ ፋይናንስ ቢሮ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ አሶሳ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 34/2019
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፋይናንስ ቢሮ በክልሉ ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ትናንሽ የመስክ መኪናዎች ያገለገሉ የህዝብ ማመላለሻ መኪናዎች፣ ያገለገለ ካት ግሬደር ያገለገለ በማንኩ ሩሌ ያገለገለ ኒው ሆላንድ ትራክተር እስከ ተሳቢው ሞተሩ የተቃጠለ ዶዘር ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች የተለያዩ አይነት ያላቸው ብረታብረቶች ያገለገሉ የመኪና ጎማዎች ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ጀኔሬተሮች፣ የመኪና ባትሪዎች ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ባህርዛፎችና ግራቪሊያ ዛፎችን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል:: በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ላገለገሉ ተሽከርካሪዎች ምድብ አንድ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ ላገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ቁርጥራጭ ብረታብረቶች፣ ጀኔሬተሮች፣ የመኪና ባትሪዎች ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ባህርዛፎች፣ እና፣ ግራቢሊያ ዛፎች እንደየ ምድባቸው የማይመለስ 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል በቤ/ጉ/ክ/መ/ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 30 በመቅረብ ሰነዶችን መግዛት ይችላሉ::
- ጨረታው ክፍት ሆኖ የሚቆየው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ብቻ ይሆናል::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ/ ለሚወዳደሩበት ንብረቶች የሚጫረቱበትን የገንዘብ መጠን የጠቅላላ ዋጋ 15% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ በቤ/ጉ/ክ/መ/ፋይናንስ ቢሮ ስም የተሰራ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው::
- ማንኛውም /****ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 30 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘውትር በስራ ሠዓት ከጠዋቱ 2:30 እስከ 11:00 ማስገባት ይችላሉ::
- ጨረታው ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ ቢሮ አዳራሽ በ16ኛው ቀን ከጧቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4:30 ሠዓት ይከፈታል::
- 16ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው የሚከፈተው ሰዓቱ እንደተጠበቀ ሁኖ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል::
- ከጨረታው ጋር በተያያዘ አለመግባባት ቢፈጠር ጉዳዩ የሚፈታው በክልሉ ውስጥ ሆኖ በክልሉ ህገ መንግስት ይሆናል::
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በሞባይል ቁጥር 0910932774 በመደወል መረዳት ይችላሉ::
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ አሶሳ
✨ messages.ai_summary
Sale of various used regional government assets: small field vehicles, public transport vehicles, a used cat grader, used Manco roller, used New Holland tractor, a bulldozer with burnt engine, used motorcycles, assorted scrap metal, used tires, used electronics, generators, car batteries, bamboo and gravilia trees. Bidders must meet stated requirements.
