የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሞዳሊቲ ለአቶ ሙሐመድ ቦራ በዱቤ ግዥና ኪራይ ያስተላለፈ ቢሆንም ደንበኛው በውሉ መሰረት የኪራይ ክፍያ ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ/ለማከራየት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት
የዝግ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሞዳሊቲ ለአቶ ሙሐመድ ቦራ በዱቤ ግዥና ኪራይ ያስተላለፈ ቢሆንም ደንበኛው በውሉ መሰረት የኪራይ ክፍያ ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ/ለማከራየት ይፈልጋል፡፡
| ተ.ቁ | የተከራዩ ስም | የሚሸጠው ንብረት ዓይነት እና ዝርዝር መረጃ | ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ | የዝግ ጨረታ መነሻ ዋጋ (በብር) | ዝግ ጨረታ የሚካሄድበት ቦታ | የዝግ ጨረታ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት | የጨረታ ሁኔታ |
| 1 | አቶ ሙሐመድ ቦራ | 1. Rotary Oven 14 Try (01) set 2.Volumetric Dough Divider የሊጥ ማከፋፈያ (01) set. 3. Mixer የሊጥ መቀላቀያ (01) set 4. Molding machine የሊጥ ቅርጽ ማውጫ (01) set 5. Brade slicer የዳቦ መቁረጫ አንድ (1) set 6. French tray with trolley ሁለት (02) set 7. Flat tray with Trolley ሁለት (02) 8. Diesel Generator አንድ (01) set ናቸው፡፡ | ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በቡርጂ ዞን፣ ሶያማ ከተማ አስ/ር፣ 02 ቀበሌ ክልል ውስጥ በተቋቋመው በአቶ ሙሐመድ ቦራ (በተከራይ) የዳቦ ማምረቻ ቦታ፤ | 7,237,089.33 | ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጋሞ ዞን፣ አርባምንጭ ከተማ በሚገኘው የዲስትሪክቱ ቢሮ | ጥቅምት 18 ቀን 2019ዓ.ም 4:00 እስከ 6:00 | ዝግ ጨረታ |
የዝግ ጨረታው መመሪያ
- በዝግ ጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ስምና አድራሻ በመጥቀስ፣ የታደሰ መታወቂያ ኮፒ፣ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ወይም 25% በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ኮፒ አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ገዢው የሚገዛበትን ዋጋ በመግለጽ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2019ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ድረስ ማመልከቻ ማስገባት ይቻላል፡፡
- ንብረቱ የሚገኘው ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በቡርጂ ዞን፣ ሶያማ ከተማ አስ/ር፣ 02 ቀበሌ ክልል ውስጥ በተቋቋመው በአቶ ሙሐመድ ቦራ (በተከራይ) የዳቦ ማምረቻ ቦታ፣ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው፡፡ የዝግ ጨረታ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) ፤ ንብረቶችን በጥሬ ገንዘብ ወይም እጅ በእጅ ሽያጭ የሚገዛ ከሆነ ከቀረጥ ነጻ መብት የመጠቀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ከሌለው በመንግስት/በሕግ የተወሰነ ታክስ ጨምሮ የሚጠየቁ ማንኛውንም ክፍያ በቅድሚያ በመክፈል ንብረቱን ይረከባል፡፡
- ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በካሽ/በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን ይረከባል፡፡በዝግ ጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል (ግለሰብ፣ተቋማት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማህበራት) ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም ተመሳሳይ መብት ያለው ከሆነ ወይም መንግስት በንብረቶቹ ላይ የሚያስከፍለውን የጉምሩክ ቀረጥ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ ሁሉ በዝግ ጨረታ መሳተፍ ይችላል፡፡
- ንብረቱን በከፊል ለመከራየት የሚፈልግ ተጫራች ከሆነ ቢያንስ ያሸነፈበትን ዋጋ 20% ቅድሚያ በመክፈልና የባንኩን የሊዝ ኪራይ መስፈርት በሟሟላት በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ የማሽነሪ ኪራይ ውል መፈረም ይኖርበታል፡፡ ሆኖም ግን በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ካልተወጣ የዝግ ተጫራች አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፡፡ለተሸነፉ ተጫራቾች በጨረታው ያስያዙት የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
- ንብረቱ በባንኩ የካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት መሰረት የመከራየት ዕቅድ ያለው ተጫራች የባንኩን ካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ በቅድሚያ አርግጠኛ መሆንና በባንኩ ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት ባንኩ የሚያከናውነው የፕሮጀክቱ ጥናት ላይ የሚቀመጡ ቅድመ-ሁኔታዎች መስማማት ይጠበቅበታል፡፡ የዝግ ጨረታ አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ንብረቱን ለማስተዳደር የሚወጡ ተያያዥ ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ ይጠበቅበታል፡፡
- የዝግ ጨረታ አሸናፊ የካፒታል ዕቃው ከለበት ቦታ ወደ ሚፈለግበት ቦታ ማጓጓዣ ወጪ፤ የጉዞ ኢንሹራንስ፤ ስራ ማስጀመሪያና ተያያዥ ወጪዎችን ገርው ይከፍላል፡፡
- የዝግ ጨረታው ተጫራቹ ወይም ሕጋዊ ወኪል በተገኙበት ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 እስከ 6:00 ሰዓት በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት ሎን ወርክ አውት ዲቪዥን ቢሮ ይደረጋል፡፡
ስለንብረቱ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 046-181-0606/0303 ደውሎ ማነጋገር ይችላል፡፡ ንብረቶቹን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከዝግ ጨረታ ቀን በፊት ባሉት ጊዜያት ቀጠሮ በመያዝ ንብረቶቹ በሚገኙበት በተከራይ ማምረቻ ቅጥር ግቢ ውስጥ በአካል በመቅረብ መጎብኘት ይቻላል፡፡
ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የዝግ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት
✨ messages.ai_summary
Ethiopia Development Bank Arba Minch District seeks to sell or lease bakery machinery (rotary oven, dough divider, mixer, molder, bread slicer, trays, generator) via closed bid after the lessee defaulted. Bidders must submit ID copy and a 25% CPO; winners pay 15% VAT unless tax-exempt.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
