Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት
  • Address አፍንጮ በር ፍቅር ኘላዛ ቢሮ ቁጥር 402 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115573176
  • Websitehttps://www.ppa.gov.et/
  • Deadline13 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price600(ስድስት መቶ ብር) / 500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityለሚገዙት የተለያዩ ተቋማት ተሽከርካሪዎችና በቁርጥራጭ መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች የጨረታ መነሻ ዋጋውን 20 በመቶ (20%)፣ ሌሎችን ንብረቶችን፣ ደግሞ የጨረታ መነሻ ዋጋውን 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ
  • opening dateበዚያኑ ቀን በ4:15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 504 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale , Used Items

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ያገለገሉና በስክራፕ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎችን፣ ማሽነሪዎችን፣ ብረታ ብረቶችንና የተለያዩ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ ተጫራቾችን ይጋብዛል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት


የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ተቋማት የሆኑ ያገለገሉ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣ በስክራፕ መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች፣ ሽገር ዳቦ መሸጫ ባሶች፣ ማሽነሪዎች፣ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ የተለያዩ ንብረቶች (የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ ከነመዳሪዎች፣ ቸርኬዎች፣ የህክምና እቃዎች፣ ጀነረተር፣ሊፍት፣ ባህርዛፎች፣ የጋርመንት ማሽኖች እና የፈርኒቸር ማሽኖች ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

  1. ተጫራቾች ከአፍንጮ በር ወደ 6 ኪሎ በሚወስደው መንገድ ፍቅር ኘላዛ ህንፃ ላይ በሚገኘው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመምጣት የተለያዩ ተቋማት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ በስክራፕ መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች፣ሽገር ዳቦ መሸጫ ባሶች፣ ማሽነሪዎች እና ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ ለእያንዳንዳቸው ዝርዝርና ብዛት የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 600.00 (ስድስት መቶ ብር)፣ እንዲሁም የተለያዩ የአገለገሉ የንብረቶች (የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ ቸርኬዎች፣ ፍላፖች፣ የህክምና እቃዎች፣ ከነመዳሪዎች፣ ባህርዛፎ፣ የጋርመንት ማሽኖች እና የፈርኒቸር ማሽኖች ዝርዝርና ብዛት የያዘ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ተገኝተው መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ስር ዋጋ በአሃዝ እንዲሁም በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 402 ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከ ሚታሸግበት ሰዓት ድረስ ተጫራቾች ሰነድን ማስገባት ይችላሉ ፡፡
  3. ተጫራቾች በአሃዝና በፊደል እንዲሁም በነጠላና በጥቅል በሰጡት ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ አገልግሎቱ ከፍተኛውን ዋጋ ወስዶ ያወዳድራል፡፡
  4. ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን በመግለጽ በመጫረቻ ሠነዳቸው ላይ መፈረም አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በአንድ መለያ ቁጥር(መደብ) ስር ያለውን ንብረት ብዛት በሙሉ መጫረት አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጁትን የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ቸርኬዎች፣ ባትሪዎች፣ ፍላፖች፣ ከነመዳሪዎች፣ የህክምና እቃዎች፣ባህርዛፎች የአንዱን መስሪያ ቤት በአይነት የተቀመጡትን በጥቅል መጫረት አለባቸው፡
  7. ተጫራቾች ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ድረስ በመሄድ ንብረቱን አይተው መጫረት ወይም ዋጋ መስጠት አለባቸው፡፡ ነገር ግን ንብረቱን ሳያዩ ቢጫረቱና ቅሬታ ቢቀርብ አገልግሎቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፡፡
  8. ለሚገዙት የተለያዩ ተቋማት ተሽከርካሪዎችና በቁርጥራጭ መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች የጨረታ መነሻ ዋጋውን 20 በመቶ (20%)፣ ሌሎችን ንብረቶችን፣ ደግሞ የጨረታ መነሻ ዋጋውን 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ሲ.ፒ.ኦ. ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
  9. የጨረታ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4:15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 504 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉልም፡፡
  11. ተሽከርካሪዎች የነበረባቸው የቦሎ ዕዳ እና የስም ዝውውር ወጪ በአሸናፊ ተጫራቾች ይሸፈናል፡፡
  12. አንድ ተጫራች አንድ ተሽከርካሪ እና ከአንድ የመ/ቤት ንብረቶች በላይ መግዛት ይችላል፡፡ ሆኖም አንድ ተጫራች ለአንድ ተሽከርካሪ፣ ለአንድ መደብ ንብረት የተለያየ ዋጋ በመስጠት መወዳደር አይችልም፡፡
  13. በመነሻ ዋጋና በታች የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡
  14. የጨረታ ሳጥን ከተዘጋ በኋላ ኮድ ወይም መለያ ቁጥር ሲጽፍ ተሳስቻለሁ ወይም ሳልጽፍ ቀርቻለሁ የሚሉ ጥያቄዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
  15. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለአገልግሎቱ ገቢ ይደረጋል፡፡
  16. ንብረቱን በ10 የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
  17. የቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን የሚጫረት ተጫራች ያሸነፋበትን በሙሉን ማንሳት አለባቸው
  18. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ ከጨረታው መውጣት ወይም የሰጠውን ዋጋ ማሻሻል ወይም መለወጥ አይችልም፡፡
  19. የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጡ ማናቸውም ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-557-86-71 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አገልግሎቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ኤጀንሲ

✨ messages.ai_summary
Addis Ababa City Government Procurement and Property Disposal Service invites bidders to a public auction of used vehicles, scrap vehicles, bread-sale stands, machinery, scrap metal and various items (tires, batteries, medical equipment, generators, lifts, garment and furniture machines). Bidders must inspect items on site and bid for the full quantity per lot.
Save Tender