Tender Detail

Tender Details

  • Company ETHIOPIAN LOTTERY SERVICE (የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት)
  • Address ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አጠገብ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-126-78-16
  • Website
  • Deadline17 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000(አንድ ሺህ ብር)
  • Bid Securityባለ ብር 50 ሎተሪ: ብር 300,000.00፤ ባለ ብር 25 ሎተሪ: ብር 350,000.00 (CPO ወይም ያልተመሠረተ የባንክ ጋራንቲ)
  • opening dateህዳር 08 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት
  • Categories Printing And Publishing

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የሚፋቁ የባርኮድድ ቢንጎ ባለ ብር 50 ሎተሪ ብዛት 40,000,000 (አርባ ሚሊዮን) እና የባርኮድድ ቢንጎ ባለ ብር 25 ሎተሪ ብዛት 64,000,000 (ስልሳ አራት ሚሊዮን) የሎተሪ ትኬቶችን በዘርፉ የህትመት ስራ ላይ ልምድና ፍላጎት ያላቸውን ድርጅቶች በዓለም አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ውድድር መሠረት አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል፡፡

ETHIOPIAN LOTTERY SERVICE (የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት)


ዓለም አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የገዥው መለያ ቁጥር: ELS/ICB/001/2026 and ELS/CB/002/2026

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የሚፋቁ የባርኮድድ ቢንጎ ባለ ብር 50 ሎተሪ ብዛት 40,000,000 (አርባ ሚሊዮን) እና የባርኮድድ ቢንጎ ባለ ብር 25 ሎተሪ ብዛት 64,000,000 (ስልሳ አራት ሚሊዮን) የሎተሪ ትኬቶችን በዘርፉ የህትመት ስራ ላይ ልምድና ፍላጎት ያላቸውን ድርጅቶች በዓለም አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ውድድር መሠረት አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል፡፡

  • ስለዚህም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ሁሉ ይህ ዓለም አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን በጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 08 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ስራ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ከኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት አራዳ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 01፣ ነባሩ ህንፃ 2ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 31 በስራ ቀናት ከሰኞ እስከ ዓርብ፣ በስራ ሰዓት ከ2:30 እስከ 6:30 ሰዓት እና ከ7:30 እስከ 11:30 ሰዓት ድረስ በመቅረብ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ስም በተከፈተ የባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000004652782 ገቢ በማድረግ ዋናውን ማስረጃ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ያለባቸው ለ40,000,000 (አርባ ሚሊዮን) ቢንጎ ባለ ብር 50 ሎተሪ ቲኬቶች ህትመት ላይ ለሚወዳደሩ ተጫራቾች ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) እንዲሁም ለ64,000,000 (ስልሳ አራት ሚሊዮን) የባርኮድድ ቢንጎ ባለ ብር 25 ሎተሪ ቲኬቶች ላይ በሚወዳደሩ ተጫራቾች ብር 350,000.00 (ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በሲ.ፒ.ኦ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ጋራንቲ ዋስትና ወይም ተመጣጣኝ የሆነና በቀላሉ ሊመነዘር የሚችል የገንዘብ አይነት ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር ዋናውን ማስረጃ በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ ጋራንቲ/ ከሚከተሉት አማራጮች ውስጥ በአንዱ ማስያዝ ይችላሉ፡፡

ሀ. ከታወቀ ባንክ በተዘጋጀ ሲ.ፒ.ኦ ወይም

ለ. ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ጋራንቲ ዋስትና

  • ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውንና የጨረታ ማስከበሪያውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ የቴክኒክና የፋይናንሻል ሰነዶችን የያዘ አንድ ዋናና አንድ ቅጂ ለየብቻው በፖስታ በማድረግና በፅሁፍ በመለየት እስከ ህዳር 08 ቀን 2019 ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ስራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  • ጨረታው ህዳር 08 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ህዳር 08 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት አዲሱ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 9 ይከፈታል፡፡ አገልግሎቱ ስለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ:- በስልክ ቁጥር +251-111-26-78-16 ደውሎ መረዳት ይቻላል፡፡

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Lottery Service seeks experienced printing firms to print 40,000,000 barcoded Bingo Birr 50 and 64,000,000 barcoded Bingo Birr 25 lottery tickets via international competitive bid. Bidders must have printing experience and submit technical and financial documents separately.
Save Tender