መ/ቤታችን የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በሥሩ ላሉት ዲስትሪክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን እና ኢንጅነሪንግ መሣሪያዎች መገልገያ ማለትም ዶዘር፣ሎደር፣ግሬደር፣ኤክስካቫተርና ሮለር ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
South Ethiopia Regional State Roads Authority (የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ደኢመባ 01/2019
መ/ቤታችን የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በሥሩ ላሉት ዲስትሪክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን እና ኢንጅነሪንግ መሣሪያዎች መገልገያ ማለትም ዶዘር፣ሎደር፣ግሬደር፣ኤክስካቫተርና ሮለር ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል። በመሆኑም፡-
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ የፋይናንሻል ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና እና አንድ ኮፒ ኦሪጂናል እና ኮፒ በማለት እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያው በተለያ ፖስታ ኦሪጅናል እና ኮፒ ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፡፡
- አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያው ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ማሽን ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር ብቻ/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በግዥ መመሪያው ላይ በተፈቀደ አቅራቢው በሚፈልገው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን
አቅ/ን/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት
የፖስታ ሳጥን ቁጥር 404
የስልክ ቁጥር 0911041447/0923690085
ዲላ ኢትዮጵያ
ደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን
✨ messages.ai_summary
South Ethiopia Regional State Roads Authority seeks eligible bidders to rent construction and engineering machinery—bulldozer, loader, grader, excavator, and roller—for its district offices. Bidders must submit a valid business or service license, VAT registration certificate, and tax payment proof. Open to any supplier regardless of nationality.
