Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፍትህ ቢሮ
  • Address ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0931561347
  • Website
  • Deadline19 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price400.00
  • Bid Securityብር 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO
  • opening dateበ16ተኛው ቀን በ4:30 ሰዓት ይከፈታል (የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን)
  • Categories Maintenance And Repair , Vehicle (Garage Service)

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ የሚገለገልበቸውን መኪናዎች ለአንድ አመት በሚቆይ ኮንትራት ለማስጠገን ይፈልጋል (የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት ግዥ)

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፍትህ ቢሮ


የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ የሚገለገልበቸውን መኪናዎች ለአንድ አመት በሚቆይ ኮንትራት ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ይፈልጋል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO)ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. በትራንስፖርት ሚኒስቴር ወይም በደ/ኢ/ክ/መ/ትራንስፖርት ቢሮ ወይም ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ CPO/ሲ.ፒ.ኦ/ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከመ/ቤቱ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በግንባር ቀርበው ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው አማካኝነት የማይመለስ 400.00/አራት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጥገና አገልግሎት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)በማካተት ኦርጅናል እና ኮፒውን የፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ /ኢንቨሎፕ በሰም በማሸግ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ተከታታይ ቀን 4:00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በግንባር በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታው ሳጥን በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4:15 ሰዓት ላይ ይታሸግና በ4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤16ተኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች በቂና ምቹ የጥገና መስጫ ቦታ ያላቸው መሆኑን ለጨረታ ኮሚቴዎች ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0931561347/0913304979 ደውለው መጠየቅ ይችላል፡፡

በደ/ኢ/ክ/መንግስት ፍትህ ቢሮ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ ሳውላ

✨ messages.ai_summary
South Ethiopia Regional Government Justice Bureau seeks vehicle maintenance/garage services for its vehicles under a one-year contract. Bidders must have a renewed trade license, VAT registration and TIN certificate, and Transport Ministry or regional transport bureau competency evidence (Grade 3+), plus adequate repair facilities.
Save Tender