የተሽከርካሪና ማሽነሪ መለዋወጫ፣ ዲኮር፣ ዘይትና ቅባት፣ ፎቶ ኮፒ፣ ህትመት፣ የኮምፒዩተር መለዋወጫና ጥገና ግዥ (8 ሎት፣ ቁጥር 02) - የምስ/ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ
በአብክመ ገንዘብ ቢሮ የምስ/ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥና ንብ/አስ/ቡድን
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 02
በአብክመ ገንዘብ ቢሮ የምስ/ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን አገልግሎት ለሚሰጣቸው ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል፡- ሎት 1. የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃ ሎት 2. የማሽነሪ መለዋወጫ እቃ ሎት 3. የተሽከርካሪ ዲኮር ሎት 4. የተሽከርካሪ ዘይቶች እና ቅባቶች ሎት 5. የፎቶ ኮፒ አገልግሎት ሎት 6. ህትመት ሎት 7. የኮምፒዩተርና ተዛማጅ መለዋወጫ እቃዎች ሎት 8. የኮምፒዩተርና ተዛማጅ እቃዎች ጥገና የእጅ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በማዕቀፍ የግዥ ስልት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፣የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በተጫራቾች የሚቀርበው የመወዳደሪያ ዋጋ ለእቃና አገልግሎት ለ45 ቀን ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት፤
- የሚገዙ እቃዎችን/አገልግሎቶች/ አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከመጫረቻ ሰነዱ ማግኘት ይቻላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመ/ቤቱ መሂ-1 በመክፈል ከፋይናንስ ቡድን ገንዘብ ያዥ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት 1. የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃ ብር 100,000(አንድ መቶ ሺህ) ሎት 2. የማሽነሪ መለዋወጫ እቃ ብር 40,000(አርባ ሺህ) ሎት3. የተሽከርካሪ ዲኮር ብር 10,000(አስር ሺህ) ሎት.4 የተሽከርካሪ ዘይቶች እና ቅባቶች ብር 50,000(ሃምሳ ሺህ) ሎት.5.የፎቶ ኮፒ አገልግሎት ብር 3,000(ሶስት ሺህ) ሎት.6 ህትመት ብር 3,000 (ሶስት ሺህ) ሎት.7. የኮምፒዩተርና ተዛማጅ መለዋወጫ እቃዎች ብር 5,000(አምስት ሺህ) ሎት.8. የኮምፒዩተርና ተዛማጅ እቃዎች ጥገና የእጅ ዋጋ ብር 3,000(ሶስት ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ገንዘብ መምሪያ በግዥ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ለእቃና አገልግሎት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚችሉ ሲሆን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን 11ኛው ቀን እስከ 4:00 ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሳጥኑም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ [ቀሪው የአንቀጹ ክፍል ከፎቶው በግልጽ አይነበብም]
- የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ/ፈሳሽ መጠቀም ወይም መፋቅ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
- ተጫራቾች መ/ቤቱ ካዘጋጀው የስራ ዝርዝር /ስፔስፊኬሽን/ ውጭ መጨመርም ሆነ መቀነስ ከጨረታ ውድድር ውጪ ያደርጋል፡፡
- [ከፎቶው በግልጽ አይነበብም - ሎት 3፣ 5፣ 6 እና 8 የአገልግሎት ቦታን የሚመለከት]
- በሎቶች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ከጨረታ ውጪ ያደርጋል፡፡
- በሎት4 የተጠቀሰው የተሽከርካሪ ዘይት እና ቅባት እቃ የማዕቀፍ የግዥ ስልትን አይከተልም፡፡
- አሸናፊ የሚለየው በሎት ጥቅል ድምር ውጤት ዝቅተኛ ዋጋ የሞላ ሲሆን በከፊል የጨረታ ሰነድ ዝርዝር ላይ ዋጋ መሙላት እንዲሁም ጠቅላላ ድምር ሞልቶ ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ወይም ውል የያዙባቸውን እቃዎችና አገልግሎት በምስ/ጎ/ዞን መምሪያዎች ባሉ የየራሳቸው ንብረት ክፍሎች ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ሙስና ላለመፈጸም ቃል የሚገቡበትን ቅጽና ሌሎች በተጫራቾች ተሞልተው እንዲቀርቡ መደረግ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነት አይወስድም፡፡
- የተጫራቾችን መመሪያ(SBD) በሰፋት ኮፒ ከግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር- 01 ላይ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ምስ/ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ በአካል በመቅረብ ምስ/ጎጃም ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ህንፃ ግራውንድ ቢሮ ቁጥር- 01 ወይም በስልክ ቁጥር 0587716817 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአብክመ ገንዘብ ቢሮ የምስ/ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥና ንብ/አስ/ቡድን
✨ messages.ai_summary
Supply of vehicle and machinery spare parts, vehicle decor, oils and lubricants, photocopy and printing services, and computer accessories and maintenance, divided into 8 lots. Bidders must hold a valid business license, commercial registration, TIN, and tax clearance; VAT registration is required if the purchase exceeds ETB 500,000.
