በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የግዥና ንብ/አስ/ጠቅ/አገ/ዳይሬክቶሬት በ2019 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
/የጨረታ ቁጥር 001/2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የግዥና ንብ/አስ/ጠቅ/አገ/ዳይሬክቶሬት በ2019 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
| ተ.ቁ | ሎቶች | የዕቃው ዓይነት | የሚጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ/CPO |
| 1 | ሎት 1 | አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ | 5,000 |
| 2 | ሎት 2 | አላቂ የጽዳት ዕቃዎች ግዥ | 3,000 |
| 3 | ሎት 3 | የደንብ ልብስ እና የፕሮቶኮል ልብስ ግዥ | 4,000 |
| 4 | ሎት 4 | ቋሚ ዕቃዎች /የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ | 10,000 |
| 5 | ሎት 5 | የመኪና /የጓግና ጌጣጌጥ ግዥ | 6,000 |
| 6 | ሎት 6 | የጥናት አገልግሎት | 100,000 |
| 7 | ሎት 7 | የማስታወቂያ አገልግሎት እና የመድረክ ዝግጅት አገልግሎት | 4,000 |
| 8 | ሎት 8 | የመኪና ኪራይ አገልግሎት | 10,000 |
| 9 | ሎት 9 | የመኪና ጥገና አገልግሎት | 5,000 |
| 10 | ሎት 10 | የህትመት አገልግሎት | 3,000 |
| 11 | ሎት 11 | የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና አገልግሎት | 3,000 |
| 12 | ሎት 12 | የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት | 500 |
መሟላት የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፦
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው መሆኑን፤
- የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆን አለበት፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ የሚችል፤
- የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ያለው፤
- የግብር መለያ ቁጥር/ Tin No ያለው።
- ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ በጽ/ቤታችን ስም CPO ማስያዝ አለባቸው ነገር ግን CPO ያላሰዘ ቢ ኖር ከጨረታ ውጪ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለማግኘት የሚችሉት ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመወዳደር ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ዕቃዎች ናሙና መቅረብ አለበት።
- ማንኛውም ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 5 የተቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ፒያሳ/ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው ማዘጋጃ ቤት የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በሚመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- አሸናፊው ድርጅት ተራቅን ያልጠበቀ ዕቃ ወይም አገልግሎት ካቀረበ በራሱ ወጪ የመለወጥ ግዴታ አለበት።
- መ/ቤቱ ካቀረበው ሰነድ ውጪ በላላ ሰነድ በአማርጭነት ማቅረብ አይቻልም። ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ፋይናንሽያል ኦርጅናል ዋጋ ሞልታችሁ በተናጠል /ለየብቻ/ እንዲሁም ቴክኒካል ኮፒ እና ፋይናንሽያል ኮፒ በፖስታ አድርጋችሁ የድርጅታችሁን ማህተምና ፊርማ በማድረግ ከተሰጠበት ጊዜ የንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተሬት ቢሮ ቁጥር 342 ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ።
- ተጫራቾች አስነተኛ ተጫራቾቹ ለምትጫረቱባቸው ዕቃዎች የጨረታ ሰነዱን በነፃ ለመውሰድ፦
ሀ. ካዳራጃችሁ መ/ቤት ደብዳቤ ማምጣት አለባችሁ፦
ለ. ሰነዱን በነፃ ለመውሰድ በመመሪያ መሰረት ለምታቀርቡት ዕቃ አምራች መሆን አለባችሁ፤ - ተጫራቾች ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዋጋ ሳይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በትክክል መሙላት አለባቸው።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈበት ዕቃ ወይም አገልግሎት ላይ ውል ሲገባ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፤እንዲሁም አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ እንደተገለጸለት ጨረታ ተከፍቶ ውጤት ከተሰጠ ከ8 የሥራ ቀናት በኋላ በመ/ቤታችን ቀርቦ ውል መግባት አለበት።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎች በተገኙበት ጋዜጣው ከወጣበት በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ታሽጎ 8:30 ይከፈታል። ነገር ግን ዘኛ ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የሥራ ቀናት ውስጥ የሚከፈት ይሆናል።
ማሳሰቢያ፦
- ተጫራቾች የቀረበው ዋጋ ግኝትን ያካተተ መሆኑንና ያላካተተ መሆኑን መግለጽ አለባቸው ይህ ካልሆነ ግን መ/ቤቱ የቀረበውን ዋጋ ግኝትን እንዳካተተ አድርጎ ይወስደዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሀግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ማዘጋጃ ቤት /ከንቲባ ግቢ ውስጥ/ ክፍለ ከተማ አራዳ ወረዳ 1 ፒያሳ ምንይልክ አደባባይ /ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን/ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0118680464 ይደውሉ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Addis Ababa City Administration City Manager's Office seeks bidders for stationery, cleaning materials, uniforms and protocol clothing, electronics, vehicles, study, advertising, event, vehicle rental and repair, printing, electronics repair, and uniform sewing services. Bidders must have a valid business license, tax compliance, VAT registration, supplier certificate, and TIN.
