Tender Detail

Tender Details

  • Company Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory (በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ)
  • Address አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የግዥ መምሪያ ቢሮ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114420688
  • Websitehttp://www.mughercement.com.et/
  • Deadline20 Oct 2026, 9:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price575(አምስት መቶ ሰባ አምስት ብር)
  • Bid Securityብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) (C.P.O) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ
  • opening dateጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
  • Categories Metals And Metal Working

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የመበየጃ ኤሌክትሮድ በገልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory (በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ)


የሀገር ውስጥ ገልፅ ጨረታ

ቁጥር ሙሲፋ/01/2019

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የመበየጃ ኤሌክትሮድ በገልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የ2018/2019 ዓ/ም የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት የታክስ ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና ኮፒ በማያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት ገርጂ የቀድሞው ኤምፔሪያል ህንፃ ከሚገኘው የፋብሪካው የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (C.P.O) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዕለቱ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡

ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በኬሚካል ኢንዲስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ

✨ messages.ai_summary
Mugher Cement Factory seeks to buy various welding electrodes through an open bid. Eligible bidders must have a renewed business license, VAT registration certificate, and taxpayer registration certificate. The factory reserves the right to cancel the bid in whole or in part.
Save Tender