የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ ለብቃት ፕሮጀክት የምሣ፣ ሪፍረሽመንት እና ውሃ አገልግሎት (ካፌና ሬስቶራንቶች) አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለብቃት ፕሮጀክት የምሣ፣ ሪፍረሽመንት እና ውሃ አገልግሎትን በአዳማ ከተማ ውስጥ የሚገኙትን ተወዳዳሪዎችን /ካፌና ሬስቶራንቶችን/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
ለተጠየቀው የሥራ አቅርቦት ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax payer registration No) ያላቸው
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በሲንቄ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1054551161121 ላይ ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ከመስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት በጽ/ቤቱ የግዢ የሥራ ሂደት ቢሮ ድረስ በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመከፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች በሚወዳደርበት ሰነድ ላይ በተሰጠው ስፔሲፊኬሽን መሰረት ብቻ ሳይጨምር ወይም ሳይቀንስ ዋጋውን መሙላት ይኖርበታል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የተጠቀሰውን ማስረጃዎች ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው የሚከፈተው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን የስራ ቀን ከሆነ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በአዳማ ከተማ ገንዘብ/ፅ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ግዢ ክፍል ውስጥ ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም መ/ቤቱ ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ በጨረታ መመሪያ በተሰጠው መሠረት የጨረታ አሸናፊነቱ በውስጥ ማስታወቂያና በስልክ እንደተገለፀ አስፈላጊውን የጨረታ ውል ከአዳማ ከተማ ገንዘብ ፅ/ቤት ጋር መፈራረም አለበት። ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ገቢ ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች ለውድድር የሚቀርበው ቫት ተጠቃሚ ሲሆን ፣ 7.5 % በክፍያ ጊዜ የሚቀነስ ይሆናል።
- መሥሪያ ቤቱ ከሚያደርገው የግዢ ውል 20 ፐርሰንት መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል መሆኑን ተጫራቹ መገንዘብ አለበት።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /መቶ ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በአዳማ ከተማ መስተዳድር የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Adama City Finance Office seeks eligible cafes and restaurants to provide lunch, refreshment, and water services under a project in Adama. Bidders must hold a valid business license, be VAT-registered with a taxpayer registration number, and provide proof of tax payment.
