Tender Detail

Tender Details

  • Company የካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
  • Address ካፋ ዞን ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 047 331 140
  • Website
  • Deadline15 Oct 2026, 9:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceለእያንዳንዱ ሎት 500.00 (አምስትመቶ ብር)
  • Bid Securityለእያንዳንዱ ሎት 80,000.00 (ሰማንያ ሺ ብር)
  • opening dateበዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡00
  • Categories Printing And Publishing , Vehicle (Garage Service) , Cloth And Shoes

የካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግ/ጨ/ቁጥር 03/2019 በ2019 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ የተለያዩ ደንብ ልብስ (ለሦስተኛ ጊዜ)፣ የቡና መፅሔት ህትመት አገልግሎት እና ደረጃ 3 የመኪና ጥገና ጋራጅ አገልግሎት (3 ሎቶች) አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል።

የካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ /ግ/ጨ/ቁጥር 03/2019

የካፋ ዞን ፋይናንስና መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞን ማዕከል ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾች በመጋበዝ እንደሚከተለው በሎት በመከፋፈል እስከ በጀት ዓመቱ ማብቂያ ማለትም እስከ ሰኔ 30/2019 ዓ.ም ድረስ፡- ሎት 1. የተለያዩ ደንብ ልብስ ለሦስተኛ ጊዜ የወጣ፣ ሎት 2 የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዓመታዊ የቡና መፅሔት ህትመት አገልግሎት እና ሎት 3 ደረጃ 3 የተለያዩ የመኪና ጥገና ጋራጅ አገልግሎትን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ፣ በጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከገቢዎች ባለስልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት ማስረጃ፣ የቫት ፣ የቲን ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት እና ሌሎች መረጃዎች ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች የጨረታ ዶክመንት ሊገዙ ሲመጡ ኦርጅናሉን እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ አቅርበው እንዲመሳከር የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡
  3. በመሆኑም ተጫራቾች ለሁሉም ሎቶች ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ካፋ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት ቀርበው በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ለተከታታይ 15 ቀናት ካፋ ዞን ፋይ/ኢኮ/ል/መመሪያ ግዥ ንብ/አስ/ሥራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO (Certified payment order) በጥሬ ገንዘብ እና በቼክ ሎቶች ለእያንዳንዳቸው ብር / 80,000.00 / ሰማኒያ ሺህ ብር/በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/ ስም በማሰራት ከኦሪጅናል ፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በሎት3. የተለያዩ ለመኪና ጥገና ለመወዳደር ደረጃ 3 ፍቃድ እና የዘመኑን የታደሰ የጋራዥ ኢንሹራንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሠነዱ ላይ በመጻፍ በሰም/በሙጫ/ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/ በመቅረብ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. የጨረታው ሳጥን በ16ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ በመክፈቻው ዕለት የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች ያለመገኘት የጨረታ መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም፡፡ 15 ተከታታይ ቀናት የተባለው ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በዓላትም ጨምሮ የሚቆጠር ነው የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን የመከፈት ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
  8. ተጫራቾች ያሸነፉበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ /performance bond/ ለማስያዝ ፈቃደኛ መሆን አለባቸዉ፡፡ አሸናፊው ድርጅት ከላይ ሎት 1- እና ለሎት 2 የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በሙሉ በራሱ ወጪ ካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አቅርቦ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡
  9. ተጫራቾች አሰሪው መጤት ያዘጋጀውን የተጫራቾች መመሪያ/የቴክኒካል/ ዶክመንት መጠይቅ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 047 331 1826 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

የካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

✨ messages.ai_summary
Kafa Zone Finance Department seeks suppliers for three lots: various uniforms, annual coffee magazine printing, and grade 3 vehicle garage services. Bidders need valid business license, tax and supplier certificates. Grade 3 garage license and insurance required for Lot 3.
Save Tender