በጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመጀመሪያ ዙር ግልፅ ጨረታ የጽህፈት መሳሪያ፣ የታሸገ ውሃ፣ የጽዳት ዕቃ እና የሞተር መለዋወጫ (4 ሎቶች) አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል።
በጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ፕ/ል/ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት የመጀመሪያ ዙር የተለያዩ ዕቃዎች ግዥ ማለትም ሎት-1 የተለያየ ጽ/መሳሪያ ሎት-2 የታሸገ ውሃ ሎት-3 የተለያዩ የጽዳት ዕቃ ሎት-4 የሞተር መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
- በዚህም መሰረት በዘረፉ የተሰማሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ሆነው ለጨረታው ውድድር ማቅረብ ያለባቸው የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር እና የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ 20,000(ሃያ ሽህ ብር) በCPO BIDBOND ወይንም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በተለያዩ ፖስታ ኦሪጅናል እና ኮፒ በማዘጋጀት የፋይናንሻል ሰነድ ዋጋ ያለስርዝ ድልዝ በጥንቃቄ ተሞልተው በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማ እና የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት በሚያስፈልግበት ቦታዎች ላይ በአግባቡ ስም በመጻፍ ኦሪጅናል እና ኮፒ ተብሎ ለየብቻ በትናንሽ ፖስታዎች ከታሸገ በኋላ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ ማህተም እና ስልክ ተደርጎበት ታሽጎ በመቅረብ በዕለቱ ለዚህ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ በሰዓቱ መግባት አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ጀምሮ በማይመለስ 200 ብር ከአ/ም/ዙ/ወ/ፋ/ፕ/ል/ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛ ቀን የጨረታ ሳጥኑ ልክ ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 5፡30 ሰዓት ላይ ወይም 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት በአ/ምንጭ/ዙ/ወ/ፋ/ፕ/ል/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ሥራ ሂደት ግዥ ኬዝ ቲም ሥራ ክፍል ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነዉ፡፡
አድራሻ ፡- የአ/ምንጭ/ዙ/ወ/ፋ/ፕ/ል/ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር 046 181 40 91 አርባምንጭ
በጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ እና ፕላን ልማት ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Procurement of stationery, bottled water, cleaning materials, and motor spare parts in four separate lots via open bid. Eligible bidders must submit a renewed business license, commercial registration certificate, VAT certificate, TIN, and a bid bond per lot.
