የጽ/መሳርያ እና የቢሮ አላቂ እቃዎች፣ የደረቅ ጭነት፣ ሻይ ቡና፣ የሆቴል ምስተንግዶ፣ የተሽከርካሪ ጥገና፣ የባህል አልባሳት እና የህትመት ውጤቶች ግዥ - ምዕራብ ኦሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
በደ/ም/ኢ/ክ/መ/ የምዕራብ ኦሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
1ኛ ዙር አስቸኳይ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
4. የተጫራቾች መመሪያ
- ገዥ ............................ገዥ
ገዥ ፈጻሚ የሚገኝበት አድራሻ
ክልል:- ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ
ዞን:- ምዕራብ ኦሞ ዞን
ከተማ:- ጀሙ
ስልክ ቁጥር:-0912368800/0921431533
- ለግዥ ገንዘብ የተገኘበት ምንጭ:-ከመንግስት ግምጃ ቤት፤ ከውስጥ ገቢ እና እርዳታ
- ከጨረታ ሰነድ ግዥ ጀምሮ ግዥ እስኪፈጸም ባለው ባለው ሂደት ውስጥ ተጫራቾች በአጭበርባሪነት፤በሙስና ተግባር የጥቅም ግጭትና የስነ-ምግባር ጉድለት ፈፅመው፤ ቢፈፅሙ ወይም መፈፀሙ ቢረጋገጥ በክልሉ የግዥ አዋጅ መሰረት ተጫራቾችን ከማንኛውም መንግስት ግዥ ማገድ እና በህግ እስከማስጠየቅ ድረስ መምሪያው መብት አለው።
- ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር እንዲችሉ ከጨረታ ሰነድ ጋር ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የህጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶች አብረው ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- ንግድ ምዝገባ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- ግብር ነፃ የከፈሉበትን ማረጋገጫ ማቅራብ የሚችል
- ለመንግስት ግዥ በአቅራቢነት ዝርዝር ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- በሎት 2 እና 5 በተሰማሩበት ዘርፍ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል ሎት2 የጭነት አገልግሎት የዘመኑ የቴክኒክ ምርመራ አልፎ ቦሎ ያለው የመድን ሽፋን ዋስትና ያለው የባለቤትነት ሊብሬ ማቅረብ የሚችል ምድቡ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እውቅና ከተሰጣቸው ባንኮች የጨረታ ማስከበሪያ CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
| ተ.ቁ | የሎት ቁጥር | የሎት ምድብ | የጨረታማስታወቂያ CPO መጠን (በብር) | ምርመራ |
| 1 | ሎት1 | የጽ/መሳርያ እና የቢሮ አላቂ እቃዎች | 5,000 | |
| 2 | ሎት2 | የደረቅ ጭነት አገልግሎት | 5,000 | |
| 3 | ሎት3 | ሻይ ቡና አገልግሎት | 2,000 | |
| 4 | ሎት4 | የሆቴል ምስተንግዶ አገልግሎት | 3,000 | |
| 5 | ሎት5 | የተሽከርካሪ መለዋወጫ ጥገና | 5,000 | |
| 6 | ሎት6 | የባህል አልባሳት | 3,000 | |
| 7 | ሎት7 | የህትመት ውጤቶች | 2,000 |
ሁሉም ተጫራች የጨረታ ዶክመንቱን 1(አንድ) ኦርጅናልና 1(አንድ) ኮፒ በፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
- የጨረታ ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ አየር ላይ 15 ተከታታይ የስራ ቀን የሚቆይ ሲሆን ከዋለበት ቀን በ15ኛው የስራ ቀን ከሰዓት 8:00 ታሽጎ በዚው ቀን 8:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል። 15ኛው ቀን ብሔራዊ ዝግ ቀን ሀይማኖታዊ በዓል ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ታሽጎ የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች በሁሉም የጨረታ ሰነዶች ላይ የድርጅት ማህተም መምታት፤በዕቃ ዝርዝር ቦታ ላይ የመወዳደሪያ ዋጋውን መሙላት ፤ኦርጅናል ዶክመንት የያዘው ፖስታ ላይ ኦርጅናል ብሎ መጻፍ ፤ስልክ ቁጥር መመዝገብ ፤እንዲሁም የተወዳደሩበት የዕቃ አይነት መመዝገብ ይኖርበታል። ተጫራቾች ይህ የጥር ማስተወቅያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሠነድ በብር 100/አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል በምዕራብ ኦሞ ዞን ገቢዎች መምሪያ ቁጥር 02 በመግባት መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በሁሉም የጨረታ ሰነዶች ላይ ሃሳብ ላይ ዋናና ኮፒ በማለት ተፈርምበት በጥንቃቄ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በታሸገ ኢንቨሎፕ በጨረታ ማስታወቅያ ከተመለከተው የጊዜ ገደብ በፊት በምዕራብ ኦሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የግዥ ንብረት አስ/ር ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 ለጨረታው የተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት።
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ(ሎት) መሠረት ዉሉ በተመለከተ ለ45 /አርባ አምስት ቀናት ዋጋ መቆየቱን ተወዳዳሪዎች በአፅኖት መረዳት ይኖርባቸዋል ።
- ጨረታው አሸናፊው በተጫራቾች መምሪያ በተጠቀሰው መሠረት የጨረታ አሸናፊነት እንደተገለጸ አስፈላጊውን ናሙና ማቅረብ ናሙናው ሲጸድቅ የጨረታ ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ጋራንቲ በማስያዝ ውል ማፈራረም አለበት ። ይህን ባይፈጽም በጨረታው አሸናፊነቱ መሠረት በጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል ።
5. ጨረታ የሚገመገምበት ስልት
- የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴ ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የዕቃ አይነት በጥሪ ማስታወቂያው ላይ የተጠቀሱትን ዝቅተኛ መወዳደሪያ መስፈርቶች እንዲነበቡ ያደርጋል።
- የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴ ለዕቃ ግዥው አይነት በተዘጋጀው የጨረታ መገምገሚያ ቃለ-ጉባኤ እያንዳንዱ ተወዳዳሪ ያቀረበውን መወዳደሪያ ዶክመንት ይመዘገባል (Technical Evaluation) ያደርጋል።
- በግምገማው ሂደት የተጠየቀውን ዝቅተኛ መወዳደሪያ መስፈርት ሙሉ ለሙሉ ያሟላ ተወዳዳሪ ከፋይናንሻል ግምገማ ውጭ ይደረጋል።
- በዕቃው ግዥ ዓይነት መወዳደሪያ መስፈርት ሙሉ ለሙሉ ያሟሉ ተወዳዳሪዎችን ያቀረቡትን መወዳደሪያ ዋጋ በመገምገም ዝቅተኛ ዋጋ እና አሸናፊ ድርጅት ይለያል።የተገኘው ዝቅተኛ ዋጋ መምሪያው የዋጋ ጥናት ባለሙያዎች የተሰበሰበው የዋጋ ጥናት ጋር በማመሳከር የተገኘውን ዝቅተኛ ዋጋ ሊያሳልፍም ፤ ውድቅም ሊያደርግ ይችላል።
- በማንኛውም መንገድ የጨረታ መገምገሚያ ስልት የማይለወጥና የማይቀየር መሆኑ ተወዳዳሪዎች በአፅኖት መረዳት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴ የቴክኒክና የፋይናንሻል ግምገማን በቃለ ጉባኤ መጠናቀቁን ሲያረጋግጥ ጨረታውን የገመገመበት ቃለጉባኤ ኮፒ በማድረግና ሙሉ የጨረታ ዶክመንቱን መምሪያው የጨረታ አጽዳቂ ኮሚቴ ያስረክባል።
- ጨረታ አጽዳቂ ኮሚቴ የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴ የገመገመበትን መንገድና ስልት ገምግሞ ካቢቃ በኃላ ማሻሻል ማስተካከል፤ መከተት መወገድ ያለባቸውን ሁኔታዎችን ካገኘ በጨረታ ገምጋሚ ጋር በጋራ በመሆን ግምገማው እንዲስተካከልና እንዲጸድቅ ያደርጋል።ይህ ሂደት ሲጠናቀቅ የአጽዳቂው ኮሚቴ ቃለ ጉባኤ ኮፒ እና ሙሉ የጨረታ ዶክመንቱን ለግዥ ቲም ያስተላልፋል።
- ግዥ ቲም ከጨረታ አጽዳቂ ኮሚቴ የደረሰውን የግምገማ ውጤት መሰረት ተጫራቾች ያሸነፉበትን የዕቃ አይነትና ዋጋ እንዲሁም አሸናፊ ድርጅት መምሪያው የፋይናንስ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት ቦርድ ላይ ይለጥፋል።
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን የዕቃ አይነት ዋጋ እንዲሁም ጨረታውን ተሳትፈው የወደቁ ድርጅቶችን የወደቁበትን ምክንያት በአድራሻቸው በደብዳቤ ያሳውቃል።
- የግምገማው ውጤት በፋይናንስ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት ቦርድ ላይ ከተለጠፈ በኃላ 3(ሶስት) ተከታታይ የስራ ቀናትን ቅሬታ አቅራቢ ድርጅት ካለ ቅሬታ የሚጠበቅበት ግዜ ይሆናል። አሸናፊ ድርጅቶች የቅሬታ ግዜ ከተጠናቀቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት7(ሰባት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለግዥው አይነት በተዘጋጀ የውል ስምምነት መፈጸም ይኖርባቸዋል።
- በስሪያቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው።
አድራሻ:- ደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/የምዕ/ኦ//ዞ/ፋ/መምሪያ
✨ messages.ai_summary
Procurement of stationery and office consumables, dry freight transport, tea and coffee, hotel accommodation, vehicle spare parts repair, cultural clothing, and printing outputs, divided into seven lots. Bidders must submit a renewed business license, commercial registration, TIN certificate, VAT registration, tax clearance, and supplier registration certificate.
