የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ፊሊፕስ ህንፃ ላይ ለዋና መስሪያ ቤት አገልግሎት የሚጠቀምበትን ቢሮ ለ2019 ዓ.ም የፅዳት አገልግሎት ግዥ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Sugar Industry Group (የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ)
የጨረታ ማስታወቂያ
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ
የጨረታ ቁጥር LP/OT/03/SIG/2019
- የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ፊሊፕስ ህንፃ ላይ ለዋና መስሪያ ቤት አገልግሎት የሚጠቀምበትን ቢሮ ለ2019 ዓ.ም የፅዳት አገልግሎት ግዥ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ ለ2018/19 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት/ የታክስ ክሊራንስ/ ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No) ሠርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ የሚመለከተው የመንግስት አካል ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች አገልግሎት ሰጪ ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን /መመዝገባቸውን/ የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 1000000888862 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መከፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ፣ ከሰዓት በፊት ከ2:00-6:00 ከሰዓት በኋላ ከ7:00-11:00 ቀጥሎ በተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ
አድራሻ አዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ
ጨለለቅ አልሳም ህንፃ ፊት ለፊት
ፊሊፕስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220
ስልክ ቁጥር +251 11 5-51 6271
አዲስ አበባ፣ኢትዮጵያ - ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 3 በተገለፀው አድራሻ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8:15 ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተመሠከረለት የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከቴክኒክ መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለስልሳ (60) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለሰላሳ (30) ቀናት ይሆናል፡፡
- ግሩፑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Sugar Industry Group seeks cleaning services for its head office in the Philips Building, Mexico area. Open to licensed, tax-compliant firms registered as government suppliers. Tender documents in Amharic available for purchase.
