በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕ/ዕዝ ሜንቴናንስ ግዥ ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ:- 1. የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች 2. የተለያዩ የተሽከርካሪ ጎማዎች እና ባትሪ 3. የተለያዩ የወታደራዊ ተሽከርካሪ አላቂ ዕቃዎች 4. የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች 5. የጋራዥ የመካኒክ የስራ ቱታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕራብ ዕዝ ሜንቴናንስ
የጨረታ ማስታወቂያ
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕ/ዕዝ ሜንቴናንስ ግዥ ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ:-
- የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች
- የተለያዩ የተሽከርካሪ ጎማዎች እና ባትሪ
- የተለያዩ የወታደራዊ ተሽከርካሪ አላቂ ዕቃዎች
- የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች
- የጋራዥ የመካኒክ የስራ ቱታ
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ሥለዚህ በዚህ ጨረታ ለመወዳደር ለምትፈልጉ ተጫራቾች አግባብ ያለው የዘመኑ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ሠርተፊኬት እንዲሁም ከግብር ሠብሳቢ ባለስልጣን ግብር መከፍሉንና በጨረታ እንዲሳተፍ የሚገልፅ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፣ በግዥ ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገበበት ሰርቲፊኬት ማቅረብ አለበት፣ በድርጅቱ ስም የተከፈተ የባንክ ስቴትመንት ማቅረብ አለበት፣ የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕ/ዕዝ ሜንቴናንስ ግዥ ቢሮ ዳንሻ/5ኛ ክ/መ/ድ ካዛ ካምፕ/ በመምጣት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡ CPO:-የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች ብር 174,000.00/አንድ መቶ ሰባ አራት ሺህ ብር/ የተለያዩ የተሽከርካሪ ጎማዎችና ባትሪ ብር 274,000.00 /ሁለት መቶ ሰባ አራት ሺህ ብር/ የተለያዩ የወታደራዊ ተሽከርካሪ አላቂ ዕቃዎች ብር 23,400.00 /ሃያ ሶስት ሺህ አራት መቶ ብር/ የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች ብር 6,950.00/ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃምሳ/ የጋራዥ ስራ ቱታ ብር 7,950.00/ሰባት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ብር/ ብቻ ጨረታው ጥቅምት 05 ቀን 2019 ዓ/ም ከረፋዱ 3:00 ሠዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 3:20 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዳንሻ /በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር 5ኛ ክ/መ/ድ ጠ/መምሪያ መሰብሰብያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለውን አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የምዕ/ዕዝ ሜንቴናንስ ግዥ
ስ.ቁ 0966314205/0914518912
